Connect with us

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለዓለም የጤና ድርጅት ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ ገለፁ

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለዓለም የጤና ድርጅት ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ ገለፁ
World Health Organization Director-General Tedros Adhanom Ghebreyesus FABRICE COFFRINI/AFP VIA GETTY IMAGES

ጤና

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለዓለም የጤና ድርጅት ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ ገለፁ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለዓለም ጤና ድርጅት እና ለተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ አረጋግጠዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለተቋሙ እና አመራሩ ያላቸውን ድጋፍ የገለፁት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአለም ጤና ድርጅት ቻይናን ማዕከል ያደረገ ነው በሚል ነቀፌታቸውን ካሰሙ በኋላ ነው፡፡

በትናንትናው እለት ከአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጠቆሙት ማክሮን፤ለድርጅቱ ሙሉ ድጋፍ የሚሰጡ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

በኮቪድ-19 ዙሪያ በቻይና እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገው ጦርነት ተገቢነት የሌለው ነው ያሉት ማክሮን፤ሀገራቸው ለተቋሙ የምታደርገውን ድጋፍ፤እና ያላትንም ታማኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል ነው የተባለው፡፡

የአለም አቀፍ ድርጅቶች ተከላካይ ናቸው የሚባሉት ፕሬዝዳንት ኢማኑዔል ማክሮን፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዓለም አቀፍ ትብብር የሚሹ ተቋማት ላይ በሚሰነዝሩት ትችቶች ላይ ከዚህ ቀደምም አፀፋ ሰጥተው ያውቃሉ፡፡

የአለም ጤና ድርጅት እና የትራምፕ የኮሮና ቫይረስ አለመግባባት ወረርሺኙ እንደተከሰተ የጀመረ ነው፡፡

የአለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 31 ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ፤አገራት ዜጎቻቸውን ለመጠበቅ እርምጃ የመውሰድ መብት እንዳላቸው ገልፆ ነበር፡፡

በዚያው ቀን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ቻይና የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ እገዳ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

ምንጭ፡ሮይተርስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top