Connect with us

አልሰምቶም ወይ ጎጃም የሳንባ ቆልፍ በሽታ መግባቱን?

#አልሰምቶም ወይ ጎጃም የሳንባ ቆልፍ በሽታ መግባቱን?
Photo Facebook

ዜና

አልሰምቶም ወይ ጎጃም የሳንባ ቆልፍ በሽታ መግባቱን?

#አልሰምቶም ወይ ጎጃም የሳንባ ቆልፍ በሽታ መግባቱን?
ይሄ በሽታ ይበልጥ ጎጃምን ያጠቃዋል!!
ቀድሞ ግን መላ ይዞ ይጠብቀዋል!!
ለምን ያጠቃዋል?

የሀገሬ አርሶ አደር አኗኗሩ ሁሉ በህብረት ነው። ሰርጉ፣ ለቅሶው፣ ክርስትናው፣ ጡት መጣባቱ፣ ሰንበቴው፣ ተስካሩና ድግሱን በህብረትና በአቆልቋይ ደግሶ በአንድ ሌማት ክብ ሰርቶ የሚበላ ደግ ህዝብ ነው። በዚህ አብሮነቱ በሚገልፅበት ሁነቶች ላይ በዚህ ሳንባ ቆልፍ (ኮሮና )ወይም ኮቪድ-19 በሽታ ዘልቆ በአንዱ ሰው ከገባ የአገሬ ህዝብ እንደክምር ጭድ ተቀጣጥሎ ይያያዛል።

የጎጃም አርሶ አደር በደቦ አርሶ በጋራ መብላትን የሚያውቅ ሲወርስ ሲወራረስ የመጣ ጠንካራ ባህል ያለው ህዝብ ነው።
በአብዛኛው ፈርሐ -እግዚያብሔር ያደረበት፤ ሰንበትን የማይሽር፤ አብልቶ አጠጥቶ የማይረካ ህዝብ ነው
ሰላምታው ጉንጭን ጨምጭሞ አገላብጦ ካልሳመ ወዳጅነቱን የገለጠ የማይመስለው፤ ሲያበላ ” አፈር ስሆን በአንድ እንጨት ስሄድ ” ብሎ በአገሩ ታቦት እየማለ ካላጎረሰህ የማይረካው የጎጃም ህዝብ ይሄ በሽታ እጥፍ ድርብ ፈተና ይሆንበታል። ክፉውን ያርቅልን። አሜን!!

እና ጎጄ አንተ ጤና አገር ደህና ሲሆን ሸጋው ባህላችን ማንም አይወስድብህምና ቀድመህ ጠብቀው
ጦር ይዞ አይመጣም በአይን አታየውም ግን በትንፋሽ ፣በንጥሻ፣ በመጨባበጥ የሚተላለፍ መድሐኒት ያልተገኘለት በሳምንት እድሜ የሚገል በሽታ መጧል። ይህ ሳንባ ቆልፍ የሆነ በሽታ ፈረንጁን ህዝብ እየጨረሰ ከደጃፍህ ደርሷል።

እናም ጎጄ ወለም ዘለም ሳትል ሰንዳ ብለህ የደብር አለቃው፣ የቀበሌው ሊቀመንበር፣የሀገርህ ሀኪም የሚሉትን ሰምተህ ተግብረው
#እጅን በሳሙና ሙልጭ አድርጎ በየ ሰዓቱ መታጠብ
# አራት ክንድ የሚሆን ከሰው ተራርቆ መቆም፣መጓዝ አሊያ መቀመጥ
# ይሄ በሽታ እስኪያልፍ ከቤት አለመውጣት ነው

መለኛው ለጊዜው የሰርጉ ድግስ፣የሰንበቴው ጥሪ፣የተስካሩና የደብሩን በጋራ መጓዙን ተወት አድርገው።
ቀድሞ መላ ይዘይዳል ስል መቼም አሉ የሉም የሚባሉ የባህል ሀኪሞች ጎጃም ሞልተዋል የሚጨስ፣ የሚዋጥ፣የሚሸተትና በክንድ የሚታሰር አግኝተውለት ይሆናል። እንግዲህ ሊቃውንት ታሪክ ስትሰሩ የነበራችሁ ተመካከሩ ። ፈረንጅ እስከ አሁን በጀ ያለው መላ የለምና።

በሰላም፣በጤና እና በቸር ያገናኘን ።
እንፀልይ!!

ደምስ አያሌው ቢሻው
ለ መጋቢት 28/2012 ዓ.ም ማዳረሻ እኩለ ለሊት

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top