Connect with us

አፍሪካ በኮሮና ምክንያት 200 ቢሊዮን ዶላር ልታጣ ትችላለች – ጥናት

አፍሪካ በኮሮና ምክንያት 200 ቢሊዮን ዶላር ልታጣ ትችላለች - ጥናት
Photo Facebook

ኢኮኖሚ

አፍሪካ በኮሮና ምክንያት 200 ቢሊዮን ዶላር ልታጣ ትችላለች – ጥናት

አፍሪካ በኮሮና ምክንያት 200 ቢሊዮን ዶላር ልታጣ ትችላለች – ጥናት

የቅርብ ጥናቶች እንዳሳዩት በአፍሪካ የኮሮና ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳት ለመቋቋም አፍሪካውያን በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

አለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት የጥናት ተቋም ማኪንሴይና የዘርፉ ባለሙያዎች ባደረጉት ጥናት አፍሪካ በወረርሽኙ የተነሳ አመታዊ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርቷ ከአምስት እስከ 8 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል በአጽንኦት ጠቁመዋል፡፡

በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ በ2020 አፍሪካ ከ90 እስከ 200 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ምጣኔ ሃብታዊ ኪሳራ እንደሚገጥማት ነው የተነገረው፡፡

ወረርሽኙ በሚያስከትለው የእንቅስቃሴ ገደብ ችግር ከሚያጋጥማቸው ዘርፎች መካከል በአፍሪካ ያሉ አለም አቀፍ የጉብኝት ስፍራዎች፣ ወደ ውጭ የሚላኩ እቃዎች አቅርቦት፣ዘይት ነክ ያልሆኑ ምርቶች፣የኢንቨስትመንት መራዘም ወይም መቋረጥ ተጠቅሰዋል፡፡

15 በመቶ የሚሆነው የችግሩ መነሻም ከነዳጅ ዋጋ ሁኔታ ጋር እንደሚያያዝ ተገልጿል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ በተለይም በነዳጅ ምርት ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችልና ችግሩ ከአገር አገር ሊለያይ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የዘርፉ ባለሙያዎች ለአፍሪካ መንግሥታትና የልማት አጋሮች የመፍትሄ ሃሳቦችን የለገሱ ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት መሪዎቹ በችግሩ ላይ በጋራ በመምከር ተጨባጭ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ጥናቱ አሳይቷል፡፡

ጥናቱ ከጠቆማቸው ምክረ አሳቦች መካከል የችግሩ ሰለባ ለሚሆኑት ሰዎችና ቢዝነስ ተቋማት ማቋቋሚያ ‹‹ የአፍሪካ የትብብር ፈንድ›› የተባለ አጋዥ ሃይል አንዱ ነው፡፡

አክሎም ከስራ የሚፈናቀሉ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡

ይልቁንም አፍሪካ ከሌሎች አለማት በሚመጣ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ከመመስረት ወጥታ በስሯ ባሉ ሌሎች አማራጮች ላይ እንድታተኩር ጥናቱ ምክረ አሳቡን ለግሷል፡፡

ምንጭ፡አናዶሉ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top