Connect with us

መድሀኒት እና ቁሳቁሶች መሰራጨት ጀመረ

መድሀኒት እና ቁሳቁሶች መሰራጨት ጀመረ

ዜና

መድሀኒት እና ቁሳቁሶች መሰራጨት ጀመረ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በቻይና መንግስት በእርዳታ የተሰጠውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የሙቀት መጠን መለኪያ (ኢንፍራሬድን) ጨምሮ ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን ማሰራጨት ጀመረ፡፡

ከ መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ከቻይና መንግስት በእርዳታ የተሰጠውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የህክምና ግብዓቶች ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች ያሰራጫል፡፡

የህክምና ግብዓቶቹ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዱ የሙቀት መጠን መለኪያ Infrared thermometer)፣ የፊት መሸፈኛ ጭምብል (protective face mask for medical use)፣ የፊት መሸፈኛ ፕላስቲክ (Medical Protective Goggles)፣ የህክምና ባለሙያዎች የሚለብሷቸው መከላከያ ልብሶች (Disposable Protective Clothing) ናቸው፡፡

እነዚህ ለኮቪድ – 19 ኮሮና ቫይረስ ለመለየትና ለመከላከል የሚውሉ የህክምና ግብዓቶችን ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ላቋቋሟቸው የህክምና ለይቶ ማቆያ ተቋማት የሚሰራጩ ሲሆን በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሰጠው የስርጭት ክፍፍል መሰረት ይሰራጫል፡፡(ጤና ሚ/ር)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top