Connect with us

እነኚህን ደግ የአዳማ ቤተሰቦች እናመሰግናለን፤ እንበላቸው

እነኚህን ደግ የአዳማ ቤተሰቦች እናመሰግናለን፤ እንበላቸው

ነፃ ሃሳብ

እነኚህን ደግ የአዳማ ቤተሰቦች እናመሰግናለን፤ እንበላቸው

እነኚህን ደግ የአዳማ ቤተሰቦች እናመሰግናለን፤ እንበላቸው፡፡
አረጋውያንን ቀድሞ ከታደግ-ያለን እስከ ማካፈል የደረሰ ፍቅር፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ
ይህ ቤተሰብ ለወትሮው የአደማ አምባደር ነው፡፡ የደግነት መገለጫ፤ አሁን ደግሞ ያን ልቡን ለህዝብ ደግ ነገር ደግሶበት ተመስግኗል፡፡ የሁሴን ልጆች ናቸው፡፡ ወንድምዬው አደም ሁሴን በእህቱ በዲዛይነሯ ሳምራዊት ሁሴን ተግባር እጅግ ተመስጦ አመስግኑልኝ አለ፡፡

ዲዛይነሯ ሳምራዊት ገና ኮሮና ወሬው ሲመጣ የፊት ማስክ በራሷ በማዘጋጀት ናዝሪት ከተማ ወደሚገኘው ፈለገ አረጋውያን በመሄድ ለአረጋውያኑ ለገሰች፡፡ ከቀናት በኋላ ገበያው ስለ ፊት ጭምብል ሲተራመስ ወቅቱን ለገበያ ያልተጠቀመችው ወጣት ይልቁንስ አረጋውያኑን ስለመታደግ ከጊዜ ጋር ግብግብ ገጥማ ደግነቷን እውን አደረገች፡፡

የሳምራዊትን ጥረት የተመለከተው ቤተሰብ ድንገት በሆነው ነገር ልቡ ተነካ እንደ እሷው ኮሮና ያመጣውን ችግር መቋቋም ይችሉ ዘንድ አረጋውያኑን አሰቡና የንጽህና ቁሳቁሶችን ገዝተው አበረከቱ፡፡

እንዲህ ያለው መልካምነት የቤተሰቡ መገለጫ ነው፡፡ ገጣሚ አደም ሁሴን ለአረጋውያን መልካም በማድረግ ይታወቃል፡፡ አዳማ ጎራ ያለ የጥበብ ቤተሰብ የዚህ ቤተሰብን ሰው መውደድ ነፍስ ዘርቶ ሲሄድ ይመለከተዋል፡፡

አዳማ የታየው ሌላው መልካምነት ናዝሪት ያፈራቻት ናዝሪት ሃይለማርያም የተባለች በጎ ሰው ርቀት ያልገደበው መልካምነት ነው፡፡ በአሜሪካን ሀገር የምትኖረው ድምጻዊት ናዝሪት ሃይለማርያም ከምትኖርበት ሀገር ስለትውልድ ቀዬዋ አስባ በአዳማ ለሚገኙት የሴዴቂያስ የአረጋውያን መርጃና ለፈለገ አረጋውያን የፈሳሽ ሳሙናዎችና የፊት ማስኮችን ለግሳለች፡፡

ደጉ ቤተሰብ የራሱን ደግነት በስውር የሰጠ እንደሚለው አድርጎ ናዝሪት ሃይለማርያምን አመስግኑልኝ አለ፡፡ እኛ ግን ሁላችሁንም እናመሰግናለን፡፡ በስውር የምታደርጉት በስም የማናውቃችሁን ደጎች ሁሉ እናመሰግናለን፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top