Connect with us

ከ3 እስከ 5 ቀናት ውሀ የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች

ከ3 እስከ 5 ቀናት ውሀ የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች
Photo Facebook

ዜና

ከ3 እስከ 5 ቀናት ውሀ የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከአቃቂ ጥልቅ ጉድጓዶች ወደ ከተማ ውሃ ይዞ የሚመጣው 800 ሚሊ ሜትር ከባድ የውሃ መስመር በድጋሚ ስብራት አጋጥሟል፡፡

ስብራቱም በለቡ አካባቢ ያጋጠመ ሲሆን ጥገና ለማከናወን ከ3 አስከ 5 ቀን ይወስዳል ።

በመሆኑም  ማለትም ከመጋቢት 21 ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 /2012 ዓ.ም ድረስ መስመሩ ተዘግቶ ጥገና የሚከናወን በመሆኑ ፤ ከታች በተገለጹ ወረዳዎች ውሃ ይቋረጣል ፡፡

ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከወረዳ 6 እስከ 15፣
አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከወረዳ 1 እከ 10፣
ጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 7 እስከ 10 እንዲሁም
ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 2 በሙሉ እና በከፊል ከ3 አስከ 5 ቀን ላላነሰ ጊዜ የውሃ አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ባለስልጣኑ የተሰበረውን ከፍተኛ የውሃ መስመር በአጭር ጊዜ ለመጠገን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ያለ ሲሆን መደበኛ የሆነው የውሃ ስርጭት እስኪስተካከል በአለም ባንክ፣ ወይብላ እና ኬ3 ተብሎ በሚጠሩት ማጠራቀሚያዋች ውሃን በቦቴ አመላልሶ በመሙላት እና ለህብረተሰቡ ለማሰራጨት ጥረት የሚደረግ መሆኑን እየገለፅን ፤በዚህ አጋጣሚ በተጠቀሱት አካባቢዎች የውሃ እጥረት ቢከሰት ደንበኞቹ ችግሩን ተረድተው እንዲታገሱት በትህትና እንጠይቃለን ሲል

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

Continue Reading
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top