Connect with us

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተጨማሪ ማብራሪያ ~ ስለኮሮና መድሀኒት

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተጨማሪ ማብራሪያ ~ ስለኮሮና መድሀኒት
Ethiopian Health Minister Dr Lia Tadesse./Photo courtesy of social media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተጨማሪ ማብራሪያ ~ ስለኮሮና መድሀኒት

ባህላዊ ህክምናን እና ሳይንሳዊ ምርምርን በማጣመር ከእጽዋት የኮሮና ቫይረስ መድሀኒት ለማግኘት ባለሙያዎች እያደረጉ ያለው ሙከራ የመጀመሪያ የቤተ ሙከራ ሂደትያለፈ ሲሆን ወደቀጣይ የምርምር ሂደቶች እንዲሸጋር የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ የጤና ሚንስቴር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተፈራርመዋል።

ምርምሩ በመድሀኒት ግኝት ሂደት መመሪያ መሰረት ብዙ ወሳኝ የምርምር ሂደቶች የሚቀሩትና ጊዜ የሚወስድ ሲሆን በቀጣይ በሚደረጉ የእንስሳትና የክሊኒካል ምርምሮች በዓለም አቀፍ እና አገር በቀል ባለሙያዎች ጥምረት የሚካሄድ ይሆናል።

ይሄ እንቅስቃሴም ሌሎች አገራትም ለበሽታው ክትባትና መድሀኒት ለማግኘት በአለም አቀፍ ደረጃ ለሚደርገው የምርምር ጥረት አንዱ አካል መሆኑን እያስገነዘብን በአሁኑ ወቅት ያለው ብቸኛ አማራጭ በሽታውን ለመከላከል በመንግስት እና በጤና ሚኒስቴር እየተወሰዱ ያሉትን እርምጃዎችን ፣ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎችንና የተሰጡ የጤና ምክሮችን መተግበር መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን ።

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top