Connect with us

ስለ ኮቪድ-19 (COVID-19) ቫይረስ ወቅታዊ መረጃ

ስለ ኮቪድ-19 (COVID-19) ቫይረስ ወቅታዊ መረጃ
Photo Facebook

ጤና

ስለ ኮቪድ-19 (COVID-19) ቫይረስ ወቅታዊ መረጃ

ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ሀይል ከጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ (John Hopkins University) የተገኘ መረጃን በመጠቀም ስለ ኮቪድ-19 (COVID-19) ቫይረስ ወቅታዊ መረጃ

1. ቫይረሱ ሕይወት የሌለውና በስብ(Fat) የተሸፈነ ነው፡፡

2. በአይን፣ በአፍንጫ ወይም ወደ አፍ ሴሎች ሲገባ ባሕርያቸውን በመቀየር የማይፈለጉና አጥፊ ሴሎችን ያራባል፡፡

3. ቫይረሱ ሕይወት ያለው ባለመሆኑና የፕሮቲን ሞሊኪዩል በመሆኑ የሚሞት ሳይሆን በራሱ ጊዜ የሚሟሽሽ ነው፡፡ የሚጠፋበትም ጊዜ የሚወሰነው በአካባቢው ባለው የሙቀትና የአየሩ እርጥበት መጠን እንዲሁም ቫይረሱ ባረፈበት ቁስ ዓይነት ነው፡፡

4. ቫይረሱ የውጫዊ አካሉ የተሸፈነበት ስብ ባይኖር ኖሮ በቀላሉ የሚፈረካከስ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሳሙናና ሳሙና ነክ የሆኑ ማጽጃዎች ሁነኛ የመከላከያ ዘዴ ናቸው የሚባለው፡፡ ምክንያቱም በሳሙና በሚጸዳበት ጊዜ የሚፈጠረው አረፋ የቫይረሱን ስብ ስለሚያጠፋው ነው፡፡ እጅን ሲታጠቡ ለ20 ሴኮንዶች መቆየት አለበት የሚባለውም ብዙ አረፋን መፍጠር ስለሚያስችል ነው፡፡ አረፋው የቫይረሱ ሽፋን የሆነውን ስብ ስለሚያሟሟው ፕሮቲን ሞሊኪዩሉ ተበታትኖ ይፈረካከሳል፡፡

5. ሙቀት ስብን ያቀልጣል፣ በመሆኑም ሲታጠቡ ከ25ዐc በላይ የሞቀ ውሃ ቢጠቀሙ፣ ልብሶችም ሆነ ሌሎች ቁሶችን ሲያጥቡ በዚህ የሙቀት ደረጃ ቢሆን በቀላሉ አረፋ የሚያወጣ በመሆኑ የበለጠ የቫይረሱን ስብ የማቅለጥ ኃይል ይኖረዋል፡፡

6. አልኮል ወይም ቢያንስ 65% የሆነ የአልኮል ድብልቅ የቫይረሱን ስብ ያቀልጣል፡፡

7. ቫይረሱን ምንም ዓይነት ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ መድሐኒት አያጠፋውም፤ ምክንያቱም እንደ ባክቴሪያ ሕይወት ያለው ባለመሆኑ፡፡

8. ቫይረሱ ግዑዝ በመሆኑ ከሰው አካል ውጭ ሲገኝ የመፈረካከሻ ጊዜው እንዳረፈበት ቁስ ዓይነት ይወሰናል፡፡ ጨርቅነት ባላቸው ቁሶች ለ3 ሰዓታት፣ በመዳብና በእንጨት ላይ ለ4 ሰዓታት፣ በካርቶን ላይ ለ24 ሰዓታት፣ ብረት ነክ በሆኑ ዕቃዎች ለ42 ሰዓታት እንዲሁም በፕላስቲክ ላይ ለ72 ሰዓታት የመቆየት ባሕርይ አለው፡፡ ለዚህም ነው ጨርቅነት ያላቸውን ቁሶች ማራገፍ ተገቢ የማይሆነው፣ ምክንያቱም ከ3 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ በራሱ የሚጠፋው ቫይረስ ጨርቁ ሲራገፍ በዓየር ላይ በመሆን ወደ አፍንጫ የመግባት አጋጣሚ ያገኛልና ነው፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top