Connect with us

ቴዲ አፍሮ ድምጹ ብቻ ሳይኾን ልቡም የኛ የኾነ ሰው

ቴዲ አፍሮ ድምጹ ብቻ ሳይኾን ልቡም የኛ የኾነ ሰው
Photo Facebook

ጤና

ቴዲ አፍሮ ድምጹ ብቻ ሳይኾን ልቡም የኛ የኾነ ሰው

ቴዲ አፍሮ ድምጹ ብቻ ሳይኾን ልቡም የኛ የኾነ ሰው፡፡
ኃይሌ ገብረሥላሴም ከፍ ላደረጋት ባንዲራ ሀገር ከፍ ያለ መልካምነቱን አሳይቷል፡፡
ብዙ ቅኖች ወደፊት እየወጡ ነው፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም
ቴዲ አፍሮ ድምጹ ብቻ አይደለም የኛ፤ ቅን ልቡም የኛ ነው፡፡ መንፈሱም የኛ ነው፡፡ ሀገርህን በዜማ ብቻ መውደድ አንድ ነገር ነው፡፡ ስንኞች በማይገልጹት ርቀት ከጥሪት ለሀገር እንካችሁ ማለት ግን በዚህ ግዜ እንደ መበለቷ ከጉድለት የመስጠት ያህል ደግነት ነው፡፡

ቴዲ አፍሮ ዛሬ ብቻ አይደለም እንዲህ ባለው ክፉ ግዜ ደግ ኾኖ መገለጥን ደጋግሞት አሳይቶናል፡፡ እውነትም እናመሰግናለን፡፡
ኃይሌ ገብረ ሥላሴም የእኛው ሰው መሆኑን ለእኛው ባደረገው ነገር አሳይቶናል፡፡ ትናንት በዓለም ፊት ያስከበራት፣ ባንዲራዋን ከፍ ያደረጋት፤ ስሙን ከስሟ ጋር ላይነጠል የገመደው ጀግና ዛሬ አለሁ ብሎ መኖሩን አሳይቷል፡፡

ብዙ ቅን ሰዎች እየወጡ ነው፡፡ ብዙ ደጋጎችን ከፊት አይተናል፡፡ ቤታቸውን እንካችሁ ያሉ፣ ሀገር ሆነው ለሀገር የቆሙ፣ ጨለማ ነው ስንል ብርሃን የሆኑ ሰዎችን አይተናል፡፡ ህይወትን ያህል ምትክ የለሽ ሀብት የለገሱ የህክምና ባለሙያዎች በዚህ ክፉ ጊዜ ከእኛ ጋር ሆነዋል፡፡ ይሄ ሁሉ መከራ ትውልድ ይተርፍ ዘንድ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ብዙ ያደረጉት መቶ ሚሊዮን ህዝብ እንዲድን ነው፡፡ ዜጎች ዛሬ የተጠየቁት ራሳቸውን እንዲያድኑ ነው፡፡ እኛ ራሳችንን ማዳን መቻላችን ሰዎች ለእኛ ያደረጉትን መልካም ነገር ውለታ መመለስ ነው፡፡ ደግ የሆኑትን ሰዎች ደግነት ለራሳችን ደግ ነገር በመመኘት ይሄንን ክፉ ቀን እንለፈው፡፡

መንግስት የሚችለውን እያደረገ ነው፡፡ ግለሰቦች የመንግስትን ያህል ገዝፈው በደግነት ታይተዋል፡፡ ጥቂቶች ሆዳም ቢሆኑም የመልካም ሰዎች ትልቅ ነገር ብዙውን ያስተሰርያል፡፡ ለሰዎች ደግ እንሁን፤ ራሳችንን እንውደድ፣ ራሳችንን መውደድ ራሳችንን በመጠበቅ ትውልድን እናድን፤ አካላዊ ንክኪን አርቀን፣ ተጠንቅቀን ነቅተን ማህበራዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top