Connect with us

ጥቂት ስለ ኮረና ቫይረስ በሕብረተሰቡ የአተገባበር ልዩነት የሚስተዋልባቸው ሁለቱ መከላከያዎች

ጥቂት ስለ ኮረና ቫይረስ በሕብረተሰቡ የአተገባበር ልዩነት የሚስተዋልባቸው ሁለቱ መከላከያዎች
Photo Facebook

ጤና

ጥቂት ስለ ኮረና ቫይረስ በሕብረተሰቡ የአተገባበር ልዩነት የሚስተዋልባቸው ሁለቱ መከላከያዎች

ኮሮና ቫይረስን ስርጭት ከምንከላከልባቸው መንገዶች ለዛሬው ሁለቱን ብቻ ነጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡

1/ እጅን በሳሙና እና በውሃ መታጠብ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያግዝ ሲሆን በኢትዮጵያም ይህ ተግባር በየአካባቢው በንቅናቄ ሲተገበር ይስተዋላል፡፡ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡

• ወጣቶች በበጎ ፈቃድ መንገደኞችን ያስታጥባሉ፡፡
• በየተቋማት በር ውሃና ሳሙና ቀርቦ ሰዎች እንዲታጠቡ ሲደረግ ይስተዋላል፡፡
• ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎችም ውሃና ሳሙናዎች ቀርበው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡
• ታዋቂ ሰዎችና መሪዎች ጭምር ትኩረት ሰጥተው ሞዴል ሆነው አሳይተዋል
• በመስሪያ ቤቶች በር ላይ በሰፊው አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል
• በታክሲዎች መጫኛና አካባቢዎች በታንከር ውሃ ቀርቦ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል
• ሳኒታይዘር ጭምር ሕብረተሰቡ እንዲጠቀም ተደርጓል

በዚህ ተግባር በኩል እንደአገር ጥሩ ግንዛቤ መፈጠሩ በተጨባጭ የሚስተዋል ሲሆን ክፍተት የሚስተዋልበትንም እንመልከት፡፡

2/ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ወረርሽኙን ለመከላከል ወሳኝ ርምጃ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ ተግባሩን ሰምቶ በመተግበር በኩል ሰፊ ክፍተት የሚስተዋልበት ተግባር ነው፡፡

ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ሲባል የሁለት የአዋቂ ሰው ርምጃ በሚሆን ርቀት ላይ ሆኖ ተግባሩን መፈጸም መቻል ማለት ሲሆን የወረርሽኙን መተላለፍ ለመግታት ወሳኝ ርምጃ ነው፡፡

• በሳልና በማስነጠስ ወደ አየር የሚረጩ የውሃ ነጠብጣቦች አማካኝነት ቫይረሱን ከመተላለፍ ይታደጋል
• በንክኪ ወረርሽኙ እንዳይተላለፍ ያግዛል
• ሌሎች አገራትም ተግብረው ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያተረፉበት ውጤታማ መንገድ መሆኑን ተገንዝቦ መተግበሩ ለራስም፣ ለወገንም፣ ለአገርም ይበጃል፡፡

አዲስ ዘመን መጋቢት 17/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top