Connect with us

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቋማት በጊዜያዊነት አገልግሎት እንዲያቆሙ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቋማት በጊዜያዊነት አገልግሎት እንዲያቆሙ ተወሰነ
Photo Facebook

ዜና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቋማት በጊዜያዊነት አገልግሎት እንዲያቆሙ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኗ ተቋማት በጊዜያዊነት አገልግሎት እንዲያቆሙ ወሰነ።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ተቋማቱ ለጊዜው አገልግሎት እንዲያቆሙ ወስኗል።

በዚህም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ የመንበረ ፓትርያርኩ ቅርሳ ቅርስ ቤተ መፅሐፍት ወመዘክር እንዲዘጋ ተወስኗል።

ከዚህ ባለፈም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስር ከአዲስ አበባ እስከ አህጉረ ስብከት መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ ስልጠና ያልጀመሩ የካህናት ማሰልጠኛዎች፣ መዋዕለ ህጻናትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ የመማር ማስተማሩ ስራ እንዲቆም ተደርጎ ደቀ መዛሙርቱና ተማሪዎች የተማሩትን በየቤታቸው እያጠኑ እንዲቆዩ ይደረጋልም ብሏል።

በተጨማሪም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅህፈት ቤት እስከ መላው አህጉረ ስብከት ፅህፈት ቤቶች ለአስቸኳይ ስራ ከሚፈለጉና ተለይተው እንዲቆዩ ከሚደረጉ ሰራተኞች በስተቀር መላው ሰራተኞች ስራቸውን በየቤታቸው እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳልፏል።(ፋና)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top