Connect with us

«ቫይረሱን ለመከላከል ቅድመ – ዝግጅት ማድረግ ካልቻልን የሚመጣውን ጫና መሸከም አንችልም፡፡»

«ቫይረሱን ለመከላከል ቅድመ - ዝግጅት ማድረግ ካልቻልን የሚመጣውን ጫና መሸከም አንችልም፡፡»
Photo Facebook

ዜና

«ቫይረሱን ለመከላከል ቅድመ – ዝግጅት ማድረግ ካልቻልን የሚመጣውን ጫና መሸከም አንችልም፡፡»

«ቫይረሱን ለመከላከል ቅድመ – ዝግጅት ማድረግ ካልቻልን የሚመጣውን ጫና መሸከም አንችልም፡፡»

የኢዜማ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም

የ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በራስ ሆቴል «ሙሉ ኃይላችንን የኮሮና ቫይረስ (COVID – 19)ን ጫና ለመቋቋም እናውለው!» በሚል መሪ ቃል ለመንግሥትና ለግል ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የኢዜማ ጋዜጣዊ መግለጫ በማኅበራዊ፣ በፖለቲካዊ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በመከፋፈል ሀገሪቱ ሊያጋጥማት የሚችለው ተግዳሮቶች በቀጣይ በሀገሪቱ ሊደረግ የሚገባውን ቅድመ ጥንቃቄ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡

ኢዜማ በመግለጫው በምዕራብ ኦሮሚያ የተዘጋው የስልክ እና የበይነ መረብ ግንኙነት በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች እራሳቸውን ከቫይረሱ ለመከላከል የሚረዳቸውን መረጃ ለማድረስ እና ከአካባቢው ወረርሺኙን በሚመለከት መረጃ ለመሰብሰብ ተግዳሮት ስለሚሆን የስልክ እና የበይነ መረብ ግንኙነቱ ወደሥራ እንዲመለስ ጠይቋል።

መንግሥት የቫይረሱ ወረርሺኝ በንግድ እንቅስቃሴ እና በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቋቋም እንዲቻል የግል ባንኮች ከሚያበድሩት ገንዘብ 27% በመመሪያ እንዲገዙ ተገደው ከነበረው የብሔራዊ ባንክ ቦንድ ውስጥ ጊዜያቸው የደረሰውን እና ሊደርስ የተቃረበውን ቦንድ ገንዘብ እንዲከፈላቸው እና ያጋጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ቀርፈው የንግዱን እንቅስቃሴ እንዲደግፉ እንዲደረግ ኢዜማ ጠይቋል። ወረርሺኙ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድርባቸው ዘርፎችን በመለየት የግብር ቅነሳ እና የሚሰበሰብበትን ጊዜ ማራዘም እንዲሁም ከባንክ የተበደሩትን ገንዘብ የሚመልሱበትን ጊዜ በማራዘም የግል ዘርፉ ወደሠራተኛ ቅነሳ እና ሥራቸውን ወደማቆም እንዳይሄድ ድጋፍ እንዲደረግም በመግለጫው ተጠይቋል።

የኢዜማ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) «በአሜሪካ ከሳምንት በፊት በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት በመቶዎች የሚቆጠሩ ብቻ ነበሩ አሁን ግን የኮሮና ተጠቂዎች 42 ሺህ ደርሰዋል።… ብዙዎቹ ሀገሮች ለዚህ የተዳረጉበት ዋነኛ ምክንያት ቅድመ ዝግጅት ባለማድረጋቸው ነው፡፡ ቫይረሱን ለመከላከል ቅድመ – ዝግጅት ካላደረግን የሚመጣውን ጫና መሸከም አንችልም፡፡ የሚያስፈልገውን ጥንቃቄ ከአሁኑ ከምር ወስደን መተግበር ካልቻልን በፍፁም ልንወጣው የማንችለው ችግር ውስጥ ነው የምንገባው። ማንኛውም ሰው አስፈላጊ ካልሆነ በቀር በተቻለ መጠን እራሱን በቤቱ ብቻ እንዲወስን ማድረግ ናቸው አደጋውን ለመቋቋም የሚረዱን» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። «አሁን በኮሮና የተያዙ 12 ሰዎች የተገኙት የተመረመሩት ብቻ ናቸው፡፡ ቁጥሩም ይሄ ብቻ ነው ማለት አይቻልም፡፡» ብለዋል፡፡

የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ የቀጣዩን ሀገር አቀፍ ምርጫና የምርጫ ቦርድን ሰሌዳ በተመለከተ «ምርጫም ፖለቲካም የሚኖረው ሰው ሲኖር ነው፡፡ እኛ ቅድሚያ ሕዝቡን ከኮሮና እንዴት ማዳን እንችላለን የሚለው ነው የሚያሳስበን፤ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት ቀርቶ ያደጉ ሀገራትም መቋቋም አቅቷቸዋል፡፡ …አሁን መንግሥት ሥርጭቱን ለመግታት ለ15 ቀን የጣላቸው ዕቀባዎች የምርጫ ቦርድ ብዙ ሥራዎች ተስተጓጉለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ምርጫ ቦርድ በያዘው እቅድ መሠረት መሄድ እንደማይችል ፓርቲዎችን ሰብስቦ ባናገረበት ወቅት ገልጿል» ብለዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • #ድሬደዋ #ድሬደዋ

  ዜና

  #ድሬደዋ

  By

  #ድሬደዋ በድሬዳዋ አስተዳደር የኮቪድ-19 ወርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በማያከብሩ ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ፡፡...

 • የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል ምላሽ

  ዜና

  የአፋር ክልል ምላሽ

  By

  የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን...

 • ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  ዜና

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  By

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር...

 • ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  ዜና

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  By

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ...

To Top