Connect with us

በከተማዋ ለረዥም ጊዜ መንገድ ዳር የቆሙ ተሽከርካሪዎችን የማስነሳት ስራ ጀመረ

በከተማዋ ለረዥም ጊዜ መንገድ ዳር የቆሙ ተሽከርካሪዎችን የማስነሳት ስራ ጀመረ
Photo: Facebook

ዜና

በከተማዋ ለረዥም ጊዜ መንገድ ዳር የቆሙ ተሽከርካሪዎችን የማስነሳት ስራ ጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ለመንገድ ትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል በየጎዳናዎቹ ላይ ያለአግባብ ለረዥም ጊዜ የሚቆሙ የንግድ ፣ በብልሽት እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ተግባር በመጀመሩ መንገድ ዳር የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ከመጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እያስነሳ ይገኛል፡፡

ኤጀንሲው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን እና ከከተማዋ የሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ደንብ ማስከበር አገልግሎት ዘርፍ ጋር በመተባበር ሲሆን የተሽከርካሪዎቹ ባለቤቶች ንብረቶቻቸውን ከመንገድ ዳር እንዲያስነሱ ከአምስት እስከ ሰባት ቀን ጊዜ ማስታወቂያ ከተለጠፈ በኃላ በክሬን የማስነሰቱን ስራ እየተከናወነ ነው፡፡

ከየመንገዱ ዳር በክሬን የሚነሱ ተሽከርካሪዎች ለሚቆዩበት ሶስት ቦታዎች የተዘጋጁ ሲሆን እስከ አሁን ስምንት ተሽከርካሪዎች ተነስተዋል፡፡

የተሽከርካሪ ባለቤቶቹ በሚሰጣቸው የጊዜ ገደብ ተሽከርካሪዎቻቸውን የማያስነሱ ከሆነ ተሽከርካሪዎቹ በሚነሱበት ወቅት ለሚደርስባቸው ጉዳቶች ኤጀንሲው ተጠያቂ የማይሆን ሲሆን ለክሬን ማስነሻ ኪራይ ክፍያ፣ ተሽከርካሪዎቹ ለሚቆዩበት ቦታ የፓርኪንግ እና የጥበቃ አገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ባለንብረቶች ይከፍላሉ፡፡

በቀጣይም በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ምክንያቶች ለረዥም ጊዜ መንገድ ዳር ቆመው የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን የማስነሳቱ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል። (የአ/አ ከተማ ኘረስ ሴክረቴሪያት)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top