Connect with us

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የምናደርገው ጥረት ሰብአዊነታችንን ሊነጥቅ አይገባም…ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የምናደርገው ጥረት ሰብአዊነታችንን ሊነጥቅ አይገባም...ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
Photo: Facebook

ጤና

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የምናደርገው ጥረት ሰብአዊነታችንን ሊነጥቅ አይገባም…ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የምናደርገው ጥረት ሰብአዊነታችንን ሊነጥቅ አይገባም…ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

”የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የምናደርገው ጥረት ሰብአዊነታችንን ሊነጥቅ አይገባም” ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ እንደሆነ ና ቫይረሱ ከየትኛውም አገር ወይም ዜግነት ጋር የተያያዘ ያለመሆኑን መገንዘብ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

ሰው የሆነ ሁሉ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆነ ያመለከተው መግለጫው፤ የችግሩ መፍትሔ የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን የመከላከልና የጥንቃቄ መመሪያ መከተል እንደሆነም አስታውቋል።

“ቫይረሱን የመከላከል ጥረታችን ሰብአዊነታችንን የሚጋርድና ርኅራሄን የሚያስጥል መሆን የለበትም” ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

”የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካል እንደ መሆናችን አንዳችን የአንዳችን ጠባቂዎች ነን፤ የበሽታ ፍርሃት ሰብአዊነታችንን ሊነጥቀን አይገባም” ሲል ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top