Connect with us

ያለመከራ መመከር ያሻናል

ያለመከራ መመከር ያሻናል
Photo: aa.com

ጤና

ያለመከራ መመከር ያሻናል

ያለመከራ መመከር ያሻናል | (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ዘጠነኛው ሰው… ተገኘ፡፡ ከወራትና ከሳምንታት በፊት ጣልያንና አሜሪካም እንዲያ ነበር፡፡ ዛሬ በነዚህ ሀገራት የሟቾች ቁጥር በመቶዎች ነው የሚቆጠረው፡፡ የአፍሪካ መልከአምድርና ድህነት በፈጠረልን እድል በሽታው የደረሰው ስለበሽታው ምንነት፣ ምልክትና የመተላለፊያ መንገድ በሚገባ (ቢያንስ ለጥንቃቄ በበቂ ሁኔታ) ከታወቀ በኋላ ነው፡፡

መንግስት ለበሽታው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ አቅሙ በፈቀደው ያስተምራል፤ የንጽህና ግብአት ለማቅረብ እየጣረ ነው፡፡ በህዝቡ ላይ የሚታየው ግን አስገራሚ ነው፡፡ የሚባለውን አድርጎ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚጥር ብዙ አይታይም፡፡ ለመማርና ግላዊና ማህበራዊ ባህሪውን ለመጠበቅ መከራ እየጠበቀ ይመስላል፡፡

ዛሬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ ተማሪዎች ፈሳሽ ሳሙናና ውሀ ይዘው ቆመው ወደ ግቢው የሚገቡትን ያስታጥባሉ፡፡ የግቢው ጥበቃ ሰራተኞች ገቢዎችን እንዲታጠቡ ይጠይቃሉ፡፡ ታጠብ ስለተባለ የሚኮሳተረው መአት ነው፤ እምቢ የሚሉትን እግረኞች መግባት ሲከለክሏቸው ይግድ ይታጠባሉ፡፡ ባለመኪኖች ‹‹አቁመን መጣን›› እያለ በዚያው ሲሸመጥጡ ማየት ያሸማቅቃል፡፡

በየከነማው መድሀኒት ቤት በር ላይ የተከማቹት ሰዎች በሽታውን መከላከል ግብአት ለመግዛት ሳይሆን፣ በበሽታው ለመበከል ቫይረሱን ፍለጋ የተሰበሰቡ ይመስላሉ፤ ተዛዝለው ተከማችተዋል፡፡ በሽታውን ፈርቶ መከላከያ ሊገዛ የመጣ ሰው፣ እንደዚያ እርስ በርስ ተጎራርሶ ማየት ግራ ይገባል፡፡ ግራ ማጋባት ደግሞ የኢትዮጵያውያን ትልቁ መገለጫ ነው፡፡ . . . እባካችሁ መከራ ሳይከምረን እንመከር፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top