Connect with us

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዙ ፈሳሽ ማጽጃዎች በከነማ መድኃኒትቤቶች እየተሸጡ ነው

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዙ ፈሳሽ ማጽጃዎች በከነማ መድኃኒትቤቶች እየተሸጡ ነው
Photo: Facebook

ዜና

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዙ ፈሳሽ ማጽጃዎች በከነማ መድኃኒትቤቶች እየተሸጡ ነው

ህብረተሰቡ ንጽህናውን በመጠበቅ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የተባለውን በሽታ እንዲከላከል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የህዝብ መድኃኒት ቤቶች(ከነማ) በፈሳሽ መልክ የተዘጋጁ የእጅ ማጽጃ ሳሙናና ሳኒተሪ በመሸጥ ላይ ናቸው፡፡

የዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች በተዘዋወሩባቸው በአዲስ አበባ ፒያሳና ስቴድየም አካባቢዎች የንጽህና መጠበቂያውን ለመግዛት የከተማዋ ነዋሪ ተሰልፎ ይታያል።

መድኃኒት ቤቶቹም ሙሉ የሰው ኃያላቸውን በመጠቀም በምዝገባ በመታገዝ ጭምር ረጃጅም ሰልፎችን ታግሶ በመጠባባቅ ላይ ያሉትን የከተማዋ ነዋሪዎች በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የንጽህና መጠበቂያዎቹ በመድሀኒት ቤቶች ውስጥ በበቂ መጠን መኖሩንና ሁሉም እንደአመጣጡ እንዲደርሰው እየተደረገ መሆኑን ዘጋቢዎቻችን ታዝበዋል።

ለአንድ ሰው አንድ ሊትር ሳኒተሪና ግማሽ ሊትር ፈሳሽ ሳሙና በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን ከመድኃኒት ቤት ኃላፊዎቹ እና ከሸማቹ ህብረተሰብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

(ኢ.ፕ.ድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top