Connect with us

ከንቲባዬ፤ “አመሰግናለሁ፡፡”

ከንቲባዬ፤ አመሰግናለሁ፡፡"
Photo: Facebook

ጤና

ከንቲባዬ፤ “አመሰግናለሁ፡፡”

ጀሶ ጋግሮ በሚያበላ፣ በሞት በሚነግድ፣ በመከራ ወቅት የሚጨክን ጎረቤት በተፈጠረበት ዘመን እንዲህ ያለ ለሰው ጎዳና የሚውል ከንቲባ ክብር ይገበዋል፡፡
****
ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ከንቲባዬ አመሰግናለሁ፡፡ በእውነት ልቤን የገዛ ተግባር ነው፡፡ ከምሰማው የማየውን አምናለሁ፡፡ ትናንት ጎዳና ላይ ወጥተው ሀገር ከጣላቸው ጋር በዓል ሲያሳልፉ፣ ትናንት የተረሱ እናቶችን አለሁ ሲሉ፣ ትናንት ከአዲስ አበባ ስፖርት ጎን ሲቆሙ፣ ትናንት ምግብ አጥተው ትምህርት አበሳ የኾነባቸውን ልጆች ካልመገብን ሲሉ፣ ትናንት ገመና የማይሸፍን ዩኒፎርም ለብሰው የሚሰቃዩ ተማሪዎችን ይህ የሀገር ገመና ነው ብሎ እንደ አባት ሲያለብሱ፣ ትናንት አድዋ የእኛ ነው ሲሉ ይሄ ሁሉ ሲሆን ከሰማሁት ያየሁት ክቡር ተግባር ነበር ዛሬም ደገሙት፡፡

እርግጥ ነው ኮረና ገባ ሲባል የዘይት ዋጋ የጨመረችብኝ ጎረቤቴ ይሄንን ተግባርዎን “ፖለቲካ ነው” ብላ ታጣጥልብኝ ይሆናል፡፡ ያ ሳኒታይዘር በአስር እጥፍ ካልሸጠኩልህ ያለኝ ባለ ፋርማሲ የእርስዎን ደስ የሚል ተግባር “ማስመሰል ነው” ይለኝ ይሆናል፡፡ አይገርመኝም፤ በእኔ ሀገር ክፋትን የሚሰራት ነው ክፋትን የሚያከፋፍላት፡፡

እርስዎን ግን አመሰግናለሁ፡፡ ኮራሁ፤ የሆነ ስልጡን ዓለም የምኖር መሰለኝ፡፡ የክፉዎችን ሀሳብ ለማክሸፍ እንዲህ ተሸክመው መዲናዋን ከተጋረጠባት ስጋት ለመታደግ ሲባዝኑ ልቤን ሞቀው፡፡ ክፉዎትን ሲነገር ሰምቻለሁ ግን አላየሁትም፡፡ ደግ ስራዎትን ግን ብዙ እቆጥራለሁ አንዱ እንዲህ ኮሮናን ለመታገል በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችን አደባባይ እንዲወጡ ከማድረግ አልፈው አደባባይ ወጥተው መዋልዎት ነው፡፡

በራሴና በህዝቤ የማልነግድ አንድ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ የሚያኮራን ተግባር የማወደስ ሞራል አለኝ፡፡ እናም አወድስዎታለሁ፡፡ አውቃለሁ ቢሮዎን ዘግተው ሪፖርትዎን በስልክ እየተቀበሉ ሀገር ሰላም ይሆን? በሚል የማያውቋትን ከተማ ተክለ ቁመና ምሽት በቴሌቨዥን መግለጫ መስጠት እንደሚችሉ ግን አላደረጉትም፤

አደባባይ ውለው የገቡት ለነዋሪው ጥቅም ነው፡፡ ነዋሪ እንዲህ ባይሆኑም ኖሮ ምርጫ አልነበረውም፤ እንዲህ ሆኖ ከማያውቅ ከንቲባ ጋር የኖረ ነው፡፡ እንዲህ መሆንዎን የፖለቲካ ትርፍ አድርጎ በሚቆጠር አይቀየሙ፤ እንዲህ ባለው ክፉ ክስተት ገንዘብ ማትረፍ የሚፈልግ ክፉ የበዛበት ነውና ሁሉ እንደ ራሱ ይመስለዋል፡፡ አንድ ነገር እነግርዎታለሁ፤ ከንቲባዬ ነዎት፤

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top