Connect with us

ግብፅ በግድቡ ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ተቋራጮች ላይ ጫና ለመፍጠር አስባለች

ግብፅ በግድቡ ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ተቋራጮች ላይ ጫና ለመፍጠር አስባለች
Photo : Facebook

ዜና

ግብፅ በግድቡ ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ተቋራጮች ላይ ጫና ለመፍጠር አስባለች

በግብጽ ፓርላማ የዉጭ ጉዳይ ኮሚቴ በነገዉ ዕለት በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ በዛሬዉ ዕለት ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል ሲል አልሀራም በድረገጹ አስነቡቧል፡፡

ነገ በሚኖረዉ ዉይይት ኮሚቴዉ ግብፅ በኢትዮጲያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ኩባያዎች ላይ መዉሰድ ስለሚኖርባት እርምጃ እንደሚመክር ተገልጧል፡፡

በኢትዮጲያ በግድቡ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ያሉ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ላይ ግብፅ እርምጃ መዉሰድ አለባት የሚሉ የፓርላማ አባላት መበራከታቸዉም በዘገባዉ ተካቷል፡፡

እነዚህ ኩባንያዎች ግብፅ ዉስጥ የመሰማራት ፍላጎት ያላቸዉና አንዳንዶቹም ኮንትራቶችን ወስደዉ ስራ ላይ የተሰማሩ ስለሆኑ ተቋራጮቹ ግብፅ ዉስጥ እንዳይቀሳቀሱ በማገድ ጫና ማሳደር እንደሚቻል የኮሚቴዉ ሊቀመንበር የሆኑት ግለሰብ መናገራቸዉንም አልሀራም አስነብቧል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ አለም ባንክ ያሉ አበዳሪ ተቋማት ጋር በመደራደርና ኢትዮጲያ በግድቡ ላይ የቀረበዉን ስምምነት እስካልተቀበለች ድረስ ምንም አይነት አለምአቀፍ ብድር እንዳታገኝ በማድረግ ጫና መፍጠር እንሚገባም አንዳንድ የፓርላማዉ አባላት ሀሳብ ማቅረባቸዉም ታዉቋል፡፡

ግብፅ በአባይ ወንዝን ላይ ያላትን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ አካል እንደሆነ የተነገረለት ይህ አዲስ ስልት ነገ በፓርላማዉ ተቀበይነት ካገኘ ግብፅ በግድቡ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ኩባንያዎችን በሀገሯ እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ በግድቡ ግንባታ እያከናወኑ ያሉትን ስራ እንዲያቆሙ ጫና የመፍጠር ሙከራ ትጀምራለች፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top