Connect with us

የፕረስ ድርጅት የቦርድ አባልነት ሹመት ያጓጓልን?

የፕረስ ድርጅት የቦርድ አባልነት ሹመት ያጓጓልን?
Photo: Facebook

ጥበብና ባህል

የፕረስ ድርጅት የቦርድ አባልነት ሹመት ያጓጓልን?

የፕረስ ድርጅት የቦርድ አባልነት ሹመት ያጓጓልን? | (ጫሊ በላይነህ በድሬቲዩብ)

ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ቦርድ አባልነት መርጠው ከላኳቸው ሰዎች መካከል ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አንዱ ነበር፡፡ እናም ሹመቱ ሰሞኑነ ለፓርላማው ሲቀርብ የተከበሩ አንዳንድ የፓርላማ አባላት ተቃወሙት፡፡ እነዚህ አባላት በእኔ ለእውነት የቀረበ ግምት በማህበራዊ ሚደያ ወሬ ሰለባ ናቸው፡፡ ብዙዎች ዳንኤልን የሚቃወሙት ብቸኛ ምክንያታቸው ዳንኤል የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ልጅ መሆኑ ብቻ ነው፡፡ ለምን ብትል ፌስቡኩ ቃላት እየሰነጠቀ፣ ቆርጦ እየቀጠለ ዳንኤል እንዲህ አለ ከሚል የጥላቻ ወሬ የዘለለ ተጨባጭ ቁምነገር አቅርቦ አላየሁምና ነው፡፡

እርግጥ ነው፤ እንኳንስ የተከበሩ የፓርላማ አባላት ቀርቶ ማንም ግለሰብ በሰለጠነ መንገድ የማይፈልገውን ነገር መቃወሙ፣ ሀሳቡን በነጻ ማንጸባረቁ ዛሬ የተጀመረ አይደለም፡፡ ነገሩን ለጥጠን ፖለቲካዊ እናድርገው ከተባለም ሕገመንግሥታዊ መብት ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ብዙዎቹ የፓርላማ አባላት በርከት ካሉት የህዝብ አጀንዳዎች ላይ አተኩረው ሲንቀሳቀሱ፣ አስፈጻሚውን አካል ወጥረው ሲይዙ ማየት ምኞቴ ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡

ይህ ፓርላማ የአዲስአበባ ነዋሪዎች የኮንደሚኒየም ዕጣ ከወጣላቸው በሀላ ግለሰቦች ባደራጁት ሰልፍ “እስቲ ትደርሱዋትና” ብለው በማስፈራራታቸው ምክንያት ከአንድ ዓመት በላይ ቤታቸውን መረከብ ሳይችሉ ሲቀሩ ምን እየተካሄደ ነው ብሎ ጠ/ሚኒስትሩን ለማነጋገርና ችግሩን በተጨባጭ ለመቅረፍ መታገል ያልደፈረ መሆኑ በግሌ ያሳዝነኛል፡፡

ይህ ፓርላማ ትላንት በአንድ ሰው የተከበብኩኝ ጥሪ ከ86 በላይ ሰዎች ለሞት ሲዳረጉ ድምጹን እንኳን ለማሰማት የቻለ አይደለም፡፡ ዜጎች መጤ ናችሁ እየተባሉ ሲፈናቀሉ አስፈጻሚውን አካል ይህ ነገር ሁሉ ሲሆን የት ነበርክ ብሎ ወጥሮ ለመሞገት አቅም ያገኘ ፓርላማ አይደለም፡፡

ይህ ፓርላማ ቤተሰቦቻቸው ለትምህርት የላኳቸው ተማሪዎች ባልታወቁ ታጣቂዎች ሲታገቱ፣ ደብዛቸው ሲጠፋ፣ የእናቶች እምባ ጉንጫቸው ላይ ሲደርቅ የፌደራል ፖሊስ ኮምሽነሩን እንኳን ጠርቶ ምን እየሰራህ ነው ብሎ ለመጠየቅ፣ በጥያቄ ለማፋጠጥ የተሳነው ነው፡፡

ይህ ፓርላማ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጽ ስትሸልልብን፣ የጦርነት ነጋሪት ስትመታ ጠ/ሚኒስትሩን ባይችል እንኳን የሚመለከታቸውን ሚኒስትሮችን፣ የተደራዳሪአ ካላትን ካሉበት በአስቸኳይ ጠርቶ ማብራሪያ እንዲሰጡበት የመጠየቅ እንኳን ሞራል ያገኘ አይደለም፡፡

ግን ይህ ሁሉ የተሳነው ፓርላማ ውስጥ፤ ቢከፍቱት ተልባ በሆነው የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ሹመት ድምጾች ጎልተው ተሰሙ፡፡ ለምን? ለመሆኑ ፕረስ ድርጅት ውስጥ ምን አለ? ወደማውቃቸው ሰዎች ስልክ መታሁ፡፡

“ለመሆኑ የአንድ የፕረስ ድርጅት የቦርድ አባል ወርሃዊ ክፍያ ምን ያህል ነው?”

ተጠያቂው ሳቅ አመለጠው፡፡

“ምነው፤ ምን የሚያስቅ ነገር አገኘህ?”

“ኸረ ተወኝ፡፡ ምግብ ለሥራ ብትለው ይሻልሃል”

“እንዴት?”

በወር ያውም ከተሰበሰቡ ብር 1 ሺ 500 ብር ይከፈላል፡፡

“ምን?”

“አዎ ያውም ከተሰበሰቡ ነው፡፡”

ደንግጪ ዝም አልኩኝ

ተጠያቂው ቀጠለ፡፡ “እኔ እስከማውቀው ድረስ ከቀድሞ የቦርድ አባላት መካከል ይኸቺንም ክፍያ ተቀብሎ የማያውቀው አንድ የቦርድ አባል ብቻ ነው፡፡ እሱም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው፡፡ ክፍያውን በራሱ የግል ምክንያት አልፈልግም በማለቱ ተቀብሎ አያውቅም” አለኝ፡፡

አመሰግኜ ተለየሁት፡፡

እንግዲህ ይህ ሁሉ ትችት፣ ይህ ሁሉ ጉንጭ ማልፋት ሲታይ በድርጅቱ ውስጥ ለመሾም አንዳች ዳጎስ ያለ ልዩ ጥቅም ያስገኝ ይሆን ብለው የሚያስቡ የዋሆችን ፈጥሮአል፡፡ እውነታው የተገላቢጦሽ ነው፡፡ 1 ሺ 500 ብር ለአበል ክፍያ ስም እንኳን አለመብቃቱን ለአንተ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል፡፡

ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ወዳጄ እንደገለጸው ነው፡፡ ክብሩን ከገንዘብ በላይ፣ ከጥቅም በላይ ካደረገ ቆየ፡፡ ሲመደብ ያለክፍያው ቢሆን ያገለግላል እንጂ እዚህም እዚያም ሳንቲም መቃረም ውስጥ እጁን አያስገባም፡፡ የዳንኤል ተቀናቃን ሆይ እውነታውን ይኸው ነው፤ እየመረረህም ቢሆን ዋጠው፡፡

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top