ከግድቡ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ መከናወኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ ያላትን ግልጽ አቋም ለተለያዩ የዓለም አገራት መሪዎች በማሳወቅ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ ማከናወኗ ተነግሯል።
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሰሞኑን በኬንያ እና በዩጋንዳ በመገኘት ለየአገራቱ መሪዎች ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ገለጻ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በግድቡ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ እያደረጉ ያለውን ውይይት እና የጋጠሙ ተግዳሮቶቹን እንዲሁም የኢትዮጰያን ግልጽ አቋም በተመለከተም ለመሪዎቹ ገለጻና ማብራሪያ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ከሁለቱ አገራት መሪዎች ጋር የነበራቸውን ውይይት ተከትሎም መሪዎቹ የጋራ አቋም መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል።
በተመሳሳይ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሰሞኑን ወደ አውሮፓ በመጓዝ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ግልጽ አቋም በማስረዳት ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚካኤል እና ለአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮንደር ለይን አድርሰዋል።
ዶ/ር ሙላቱ በአውሮፓ በነበራቸው ቆይታ ወደ ፈረንሳይ በማቅናት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ ተመሳሳይ መልዕክት ለፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን አድርሰዋል።
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ባለስልጣናት የልኡካን ቡድን ለተመሳሳይ ተልዕኮ በቅርቡ ወደ አሜሪካ በማቅናት ከህዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ግልጽ አቋም ለመሪዎቹ እንደሚያስረዳ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር እኤአ በ2015 በደረሰችው የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት (DOP) መሰረት ከግድቡ ግንባታ ጎን ለጎን በቅርቡ የመጀመሪያውን ዉሃ በመሙላት ሀይል ለማመንጨት የሚያስችል አስፈላጊ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኗን ከሚንስቴር መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተመሳሳይ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሰሞኑን ወደ አውሮፓ በመጓዝ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ግልጽ አቋም በማስረዳት ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚካኤል እና ለአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮንደር ለይን አድርሰዋል። ክቡር ዶ/ር ሙላቱ በአውሮፓ በነበራቸው ቆይታ ወደ ፈረንሳይ በማቅናት ከጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ ተመሳሳይ መልዕክት ለፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ክቡር ማክሮን አድርሰዋል።
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ባለስልጣናት የልኡካን ቡድን ለተመሳሳይ ተልዕኮ በቅርቡ ወደ አሜሪካ በማቅናት ከህዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ግልጽ አቋም ለመሪዎቹ እንደሚያስረዳ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር እኤአ በ2015 በደረሰችው የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት (DOP) መሰረት ከግድቡ ግንባታ ጎን ለጎን በቅርቡ የመጀመሪያውን ዉሃ በመሙላት ሀይል ለማመንጨት የሚያስችል አስፈላጊ ስራዎችን በማከናወን ላይ ትገኛለች።