Connect with us

ግብፃዊያን በአሜሪካ ግድቡን በተመለከተ ዘመቻ ጀምረዋል

ግብፃዊያን በአሜሪካ ግድቡን በተመለከተ ዘመቻ ጀምረዋል
Photo : Facebook

ዜና

ግብፃዊያን በአሜሪካ ግድቡን በተመለከተ ዘመቻ ጀምረዋል

የህዳሴዉን ግድብ ግነባታ በተመለከተ በሀገራቱ መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት ተከትሎ የግብፅ መንግስት በኢትዮጲያ ላይ ጫና ለማድረግ እየሄደባቸዉ ያሉ የተለያዩ ሙከራዎች እንዳሉ ሆኖ የግብፅ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በበኩላቸዉ በያሉበት ሀገራት ተመሳሳይ ጥረቶችን ማድረጋቸዉን ተያይዘዉታል፡፡

በሀገረ አሜሪካ የሚኖሩ ግብፃዊያን ዲያስፖራዎች ግብፅ በአባይ ዉሃ ላይ ያላትን የተጠቃሚነት መብት ለመጠበቅ ያስችላል ያሉትን የበይነ መረብ ዘመቻ መጀመራቸዉን አልአህራም የተባለዉ የሀገሪቱ ዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

እንደ ዘገባዉ ከሆነ በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ግብፃዊያን ምሁራንና ባለሙያዎች የአሜሪካ መንግስት ግብፅ በህዳሴዉ ግድብ ላይ እያደረገች ያለዉን ድርድር መደገፉን በመቀጠል በድርድሩም የግብፅ ተጠቃሚነት መረጋገጥ እንዳለበት የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ መጀመራቸዉ ታዉቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ግብፃዊያኑ በዋሽንግተን የዋይት ሀዉስ ህንፃ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ እንደተዘጋጁም ተገልጧል፡፡ በተጨማሪም የግድቡ መገንባት የግብፅን የዉሃ ፍላጎት ምን ያህል እንደሚጎዳ ያሳያል ያሉትን ሰነድ ለዋይት ሀዉስ ባለስልጣናት እንደሚያስረክቡም ዘገባዉ አስነብቧል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top