Connect with us

አየር መንገዳችን ላይ አፋችንን መክፈት ትተን፤ በመከላከያው አፋችንን ብንጋርድ

አየር መንገዳችን ላይ አፋችንን መክፈት ትተን፤ በመከላከያው አፋችንን ብንጋርድ፤
Photo: Ethiopian Airlines

ጤና

አየር መንገዳችን ላይ አፋችንን መክፈት ትተን፤ በመከላከያው አፋችንን ብንጋርድ

አየር መንገዳችን ላይ አፋችንን መክፈት ትተን፤ በመከላከያው አፋችንን ብንጋርድ፤
አየር መንገዱ ላይ ጣታችን ለመቀሰር ከመሞከር ጣታችን ቶሎ ቶሎ መታጠብ፤ ጃፓናዊው የመጣው ከቡርኮናፋሶ እንጂ ከቻይና አይደለም፤ ይልቁንስ ጠማማውን ከሚያስበው ቫይረስም እንጠበቅ፤
****
ከስናፍቅሽ አዲስ
ዛሬ ደስ የማይለውን ዜና ጤና ጥበቃ ነግሮናል፡፡ እርግጥ ነው የኢትዮጵያ በራፍ በቅጡ አልተጠበቀም፡፡ ኤርፖርት ያለው ክትትል አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ብዙ ሰዎች የደነገጡት ስለ ቫይረሱ የሰማነው ክፉውን እንጂ የምንከላከልበትን ትምህርት ባለመሆኑ ነው፡፡

አንዳንድ ወገኖች አየር መንገዱ ጭኖ እንዳመጣው እንግዳ ቆጥረውታል፡፡ ህዝቡን ከማንቃት ስለ መከላከል ከማውራት ይልቅ እንዴት እንደገባ ካልተነተንኩ የሚለው በዝቷል፡፡ አየር መንገዳችን ላይ አፍን መክፈት አይጠቅመንም፤ አፋችንን መሸፈኑ ግን ባይሆን ከቫይረሱ ይጠብቀን ይሆናል፡፡

ጣት መቀሰር ባህላችን ሆነ፡፡ በዚህ ጭንቅ ሰዓት ብዬ ነበር የእከሌ ስህተት ነው ለማለት የሚደረገው ሩጫ የደረስንበትን የውድቀት ማጥ ያሳየናል፡፡ ወደ አየር መንገዱ ጣት ከመቀሰር ይልቅ ጣትን በሳሙና ደጋግሞ መታጠብ ከቫይረሱ ይታደገናል፡፡

ቫይረሱን አስገባው የተባለው ጃፓናዊ የመጣው ከቡርኪናፋሶ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲወቀስ የነበረው ወደ ቻይና በመብረሩ ነው፡፡ ወደ ቻይና በረራ ያቆሙ ሀገራት መሪዎቻቸው ጭምር ከቫይረሱ አልዳኑም፡፡ ጥንቃቄው ላይ ማውራት አለመቻላችን አጋጣሚውን ፈጥሯል፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም ሁሉ በሯን ትዝጋ ከሆነ ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ ከሚያስበው ጋር አብሮ መቆጠርም ከባድ ነው እንኳን ተወያይቶ መተማመን፤ ይሄ ችግር በቻይና የገባ ቢሆን በአየር መንገዱ ቤተሰብ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ወቀሳ ሳስብ የምንፈልገው መጠላለፍ እንጂ መዳን እንዳልሆነ እንዳስብ አስገድዶኛል፡፡ አሁንም መረጋጋት ነው፡፡ በጥንቃቄ ችግሩን ለመቆጣጠር ከሞከርን ያለመግባት ያህል ገና ሰፊ እድል ያለን ሀገር ነን፡፡

የጤና ባለሙያዎችን ምክር መስማት አደባባይ የሚያውሉ ሆታዎችን መቀነስ፣ የብልጽግና ስልጠና ጨምሮ የስብሰባ ቀጠሮዎችን አስገዳጅ ካልሆኑ ማሸጋገር የግድ ይላል፡፡ ያ ቀሺም ስፖርታችንም ጦስ እንዳያመጣ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቃታል፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top