Connect with us

ወፍሪ ሓርነት አሁንም የትግራይ ተወላጆች በእስር ላይ ይገኛሉ አለ

ወፍሪ ሓርነት አሁንም የትግራይ ተወላጆች በእስር ላይ ይገኛሉ አለ
Photo: Facebook

ዜና

ወፍሪ ሓርነት አሁንም የትግራይ ተወላጆች በእስር ላይ ይገኛሉ አለ

በመንግስት በኩል እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው 14 የትግራይ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እስካሁን የተለቀቁት 11 ብቻ መሆናቸውን ወፍሪ ሀርነት አስታወቀ።

ወፍሪ ሀርነት በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ የትግራይ እስረኞችን መብት ለማስከበር የተቋቋመ ኮሚቴ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች፦

• መንግስት የካቲት 16 ቀን 2012 ምሽት ላይ እንዲፈቱ ውሳኔ የተላለፈላቸው 14 ሲሆኑ የተለቀቁት 11 ብቻ ናቸው።

• የተፈቱትም ቢሆን በተንጠባጠበ መልኩ የተለቀቁ ናቸው። ይህ ሂደት ግልፅኝነት የጎደለው እና የታሳሪ ቤተሰቦችን ያሳቀቀ ተግባር ነው።

• መንግስት በወቅቱ ያወጣቸው በነበሩ መረጃዎች 60 ትግራዋይ የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ የሚያመላክት የነበረ ቢሆንም እንዲፈቱ ትዕዛዝ የተላለፈላቸው ግን 14 ብቻ ናቸው።

• መንግስት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ካሳለፈላቸው 61 እስረኞች ውስጥም 3 ያልታሰሩ የነበሩ እንዲሁም ሁለቱ ከዚህ በፊት ታስረው ከተፈቱ አንድ ዓመት ያለፋቸው፣ ሰባቱ ደግሞ ጥቅምት ታስረው አሁን የተፈቱ ናቸው።

• ለውጥ ላይ ነን እየተባለ አሁንም ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትግራይ የፖለቲካ እስረኞች በፌደራል፣ በክልሎች እና በሌሎች ድብቅ እስር ቤቶች ላለፉት ሁለት ዓመታት ታስረዋል፤ መንግስት እነዚህን እስረኞች ሊፈታ ይገባል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top