Connect with us

በቂ የምግብ ዋስትና አለመኖር ያለጊዜ የመሞት እድልን ይጨምራል-ጥናት

በቂ የምግብ ዋስትና አለመኖር ያለጊዜ የመሞት እድልን ይጨምራል-ጥናት
Photo: Facebook

ጤና

በቂ የምግብ ዋስትና አለመኖር ያለጊዜ የመሞት እድልን ይጨምራል-ጥናት

በቂ የምግብ ዋስትና አለመኖር ያለጊዜ የሚከሰት ሞትን እንደሚጨምር አንድ ጥናት አመለከተ ፡፡

ጥናቱ የምግብ ዋስትና አለማረጋገጥ ወይንም በቂ ምግቦችን ለማግኘት ገንዘብ አለሞኖር ያለእድሜ ለሚከሰት ሞት ምክንያት መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

በካናዳ የተጠናው ይህ ጥናት ከፈረንጆቹ 2005 እስከ 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ በካናዳ በሚኖሩ ከ510 ሺህ በላይ ጎልማሳዎች የተሳተፉ ሲሆን በዚህም 25 ሺህ ያህል ሰዎች ያለ ዕድሜ መሞታቸውን ጥናቱ ተመላክቷል፡፡

ጥናቱ እንዳመለከተው በቂ ምግብ ከሚያገኙ አዋቂዎች ጋር ሲነፃፀር የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ሰዎች ከ 10 በመቶ እስከ 37 በመቶ የሚሆኑት ከካንሰር በስተቀር በማንኛውም ምክንያት ቀደም ብለው እንደሚሞቱም አረጋግጧል፡፡

በተላላፊ በሽታዎች ፣ ድንገት በሚከሰቱ አደጋዎች እና ራስን በማጥፋት ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ሰዎች ላይ በሁለት እጥፍ ከፍተኛ መሆኑንም ጥናቱ አመልክቷል፡፡

በምግብ ዋስትና እጦት ያለ ዕድሜያቸው የሚሞቱት አዋቂዎች የምግብ ዋስትናቸው አስተማማኝ ከሆኑት ጋር ሲነጻጸር በ9 ዓመት ቀድመው እንደሚሞቱ ነው የተጠቆመው፡፡

ምንጭ፡-ዩ ፒ አይ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top