Connect with us

አቢ ሳኖ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ

አቢ ሳኖ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

አቢ ሳኖ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ

ያለፉትን ወራት በቀውስና በውዝግብ ያሳለፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት እንደተሾመለት ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። አዲሱ ፕሬዝዳንት አቢ ሳኖ ትናንት የሹመት ደብዳቤ የደረሳቸው ሲሆን ዛሬ ሥራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

አቶ አቢ ሳኖ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እንዲሁም የባንኮች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ነበር። በቀደሙት አመታትም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በነበራቸው የአመራርነት ድርሻ በብቃታቸው ከበሬታን ያገኙ ባለሙያ እንደነበሩ ያነጋገርናቸው የባንክ ባለሙያዎች ነግረውናል።

በ2010 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትነት ከተሾሙ ጀምሮ ብዙ ውዝግብ የተነሳባቸው አቶ ባጫ ጊና ፣ የቀድሞ የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ለንግድ ባንኩ አዲስ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸው ከተሰማ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከባንኩ ፕሬዚዳንትነት ተነስተው ከሌሎች የቀድሞ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር ለአምባሳደርነት መሾማቸው ተሰምቷል።

አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍጹም አስፋው የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበርነትን ከተረከቡና ገና አንድ የቦርድ ስብሰባ ማድረጋቸው ከተሰማ በሁዋላ ነው አቶ ባጫ ጊና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትነት መነሳታቸው የታወቀው። ከሀላፊነት የመነሳታቸው መነሻም በአዲሱ የቦርድ ሊቀመንበር የተደረገ ግምገማ እንደሆነ ሰምተናል። (ምንጭ፡-ዋዜማ ራዲዮ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top