Connect with us

ዛሬም በአፋር ምድር አዳዲስ የአርኪዎሎጂ ግኝቶች ይፋ እየሆኑ ነው

ዛሬም በአፋር ምድር አዳዲስ የአርኪዎሎጂ ግኝቶች ይፋ እየሆኑ ነው
Photo: Science Advances

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ዛሬም በአፋር ምድር አዳዲስ የአርኪዎሎጂ ግኝቶች ይፋ እየሆኑ ነው

በጎና መካነ ቅርስ የድንጋይ መሳሪያዎችና የሆሞ ኢሬክተስ ጭንቅላት መገኘቱን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
****
የሰው ዘር መገኛ ያስባለችንን ሉሲን ጨምሮ በርካታ ቅሪተ አካላት በአርኪዎሎጂ ቁፋሮ የተገኙበት የአፋር ምድር አሁንም አዲስ ግኝት ይፋ እንደሆነበት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ይፋ አድርጓል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በትናንትናው እለት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት አፋር ክልል ጎና መካነ ቅርስ ኦልዶዋን አሹሊያን የድንጋይ መሳሪያዎች ከሆሞ ኢሬክተስ የጭንቅላት ቅሪተ አካላት ጋር ተገኝቷል፡፡

በዚህ ስፍራ የተገኘው የሆሞ ኢሬክተር የጭንቅላት ቅሪት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ ከተገኙት የሆሞ ኢሬክተስ የቅድመ ሰው ዝርያ ቅሪተ አካላት አነስተኛ የሆነ የራስ ቅል ቅሪተ አካል ነው፡፡ ይህ ቅሪተ አካል የአንጎል መጠኑ 590 CC ነው ይላል የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መግለጫ፡፡ ይህ የምርምር ውጤት ይፋ መግለጫም ከቅሪተ አካሉ ጋር የተለያዩ የድንጋይ መሳሪያዎችም አብረው እንደተገኙ ይገልጻል፡፡

የግኝቱ መካነ ቅርስ በሆነው የጎና አርኪዎሎጂ ስፍራ የሚደረገውን ጥናት የሚያጠኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶክተር ስለሺ ሰማው እና በአሜሪካ ሀገር የሚገኘው ሳውዘርን ኮኔክቲከት ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪው ዶክተር ማይክል ሮጀርስ ናቸው፡፡

በዚሁ ስፍራ የተገኙት የሆሞ ኢሬክተስ የራስ ቅሎች ሁለት ሲሆኑ አንዱ ሙሉ የራስ ቅል የ1.5 ሚሊዮን አመታት እድሜ ያለው ሲሆን ጎና ዳና አውሌ ተብሎ በሚጠራው ወንዝ ያገኙት አሁን በህይወት የሌሉት አቶ ኢብራሂም ሀቢብ የሚባሉ አፋር ናቸው፡፡
የጎና መካነ ቅርስ ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ከተገኘችበት የሀዳር መካነ ቅርስ አቅራቢ የሚገኝ ስፍራ ሲሆን ይህ አዲስ ግኝት ሳይንስ አድቫንስ በተባለው ዓለም አቀፋዊ የኦንላይን ህትመት ይፋ ኾኗል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top