Connect with us

ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአምባሳደርነት ተሾሙ

ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአምባሳደርነት ተሾሙ
Photo: Facebook

ዜና

ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአምባሳደርነት ተሾሙ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት የሚከተለውን ሹመት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ብርሀኑ ፀጋዬ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ የቀድሞ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ የአለም ፀጋዬ፣ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች ወ/ሮ ሒሩት ዘመነ እና አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኘረዝደንት አቶ ባጫ ጊና እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት
1. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
2. ወ/ሮ የአለም ፀጋዬ
3. ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ
4. አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ
5. አቶ ባጫ ጊና
6. አቶ ይበልጣል አዕምሮ
7. አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ
8. አቶ ነብያት ጌታቸው
9. አቶ ተፈሪ መለስ ተሹመዋል፡፡

እንዲሁም
1. አቶ አድጐ አምሳያ
2. አቶ ጀማል በከር
3. አቶ አብዱ ያሲን
4. አቶ ለገሠ ገረመው
5. ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማርያም እና
6. አቶ ሽብሩ ማሞ

በአምባሳደርነት ማዕረግ መሾማቸውን የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top