Connect with us

ሐረር ቢራ የኢትዮጵያ ጥራት ልዩ ተሸላሚ ሆነ

ሐረር ቢራ የኢትዮጵያ ጥራት ልዩ ተሸላሚ ሆነ

ዜና

ሐረር ቢራ የኢትዮጵያ ጥራት ልዩ ተሸላሚ ሆነ

(ፎቶ፡- የድርጅቱ የበላይ ጠባቂና የቦርድ አባላት)

ሐረር ቢራ የኢትዮጵያ ጥራት ልዩ ተሸላሚ ሆነየ7ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተቀበሉ፡፡ በዘንድሮው ውድድር ባህርዳር የሚገኘው የጋምቢ ሆስፒታል አሸንፏል፡፡ ለሶስት ጊዜ በተከታታይ በማሸነፍ ደግሞ ሐረር ቢራ የልዩ ሽልማት ባለቤት ሆኗል፡፡

ተሸላሚዎቹን “እንኳን ደስ አላችሁ” ፤በውድድሩ ለተሳተፉት ደግሞ ምስጋና ያቀረቡት የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ክብርት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ “ያለንበት ዘመን ተኝቶ ማደርን ሣይሆን አዳዲስ እውቀት ፍለጋን ፤ ይበቃል ሳይሆን አሁንም ገና ነው ማለትን፤ ማንም አይደርስብኝም ብሎ ተኩራርቶ መቀመጥን ሳይሆን አዳዲስ ተፎካካሪዎች እየመጡብኝ ነው ብሎ ራስን ማዘጋጀትን በጥብቅ ይፈልጋል ” ብለዋል፡፡ በመሆኑም በጥራት ጉዳይ ተመሳሳይ ሀገራዊ እይታ እንዲፈጠር በማድረግ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ሁሉም አካላት በትጋት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት፣ የተመሠረተበትን ዐሥረኛ ዓመት ክብረ በዓል፣ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት እና የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ፣ ክብርት ሣህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በስካይላይት ሆቴል ማክበሩ ይታወሳል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top