Connect with us

የቴዲ አፍሮ መልዕክት “አመሰግናለሁ”

የቴዲ አፍሮ መልዕክት "አመሰግናለሁ"
Photo: Facebook

ጥበብና ባህል

የቴዲ አፍሮ መልዕክት “አመሰግናለሁ”

ለተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ በሙሉ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ <<ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር >> በሚል አላማና ስያሜ ተካሒዶ በነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ከሸገር አዲስ አበባ እና ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እንዲሁም ከባህር ማዶ ተገኝታችሁ በዝግጅታችን ላይ ለታደማችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ከልብ የመነጨ ከፍያለ ምስጋናዬን ሳቀርብ በእለቱ በቦታው ተገኝታችሁ ላሳያችሁት እና ላስመሰከራችሁት የሚያኮራ ፍፁም ኢትዮዽያዊ ጨዋነትና ለሰጣችሁን የማይለካ ፍቅር ያለኝን አክብሮት እና አድናቆት ስገልፅ በታላቅ ትህትና ነው::

በዚህ አጋጣሚ ይህ ዝግጅት ያማረ እንዲሆን ላስተባበሩት ላየንስ ፕሮሞሽን ( Lions Promotion & Entertainment ) እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስፈላጊውን እና ተገቢውን ፍቃድ በመስጠት ላደረገልን ቀና ትብብር እንዲሁም ዝግጅቱ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ተግባር በአግባቡ ለተወጣችሁ አካላት በሙሉ ከፍያለ ምስጋናዬን በራሴና በሞያ አጋሮቼ አቦጊዳ ባንድ ስም ለማቅረብ እወዳለሁ ።

ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top