Connect with us

ለቀድሞው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ ወልዱ ይመስል አሸኛኘት ተደረገ

ለቀድሞው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ ወልዱ ይመስል አሸኛኘት ተደረገ

ዜና

ለቀድሞው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ ወልዱ ይመስል አሸኛኘት ተደረገ

በሚዲያ ተቋም መሪ ታሪክ ሰራተኞች ገንዘብ በማዋጠት አመስግነው የሸኟቸው መሪ ኾነዋል፡፡ ከ240 ሺ ብር በላይ ስጦታም ተበርክቶላቸዋል፡፡

ከህወሃት ክፍፍል በኋላ የቀድሞውን የሬዲዮ ፋና ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ገሠሠን ተክተው የሬዲዮ ፋና ሃላፊ የኾኑት አቶ ወልዱ ይመስል ረዥም ዘመን ሚዲያ የመሩ ሰው ናቸው፡፡ አቶ ወልዱ ሬዲዮ ፋናን በኃላፊነት ተረክበው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተቋሙን መርተዋል፡፡ የፋና ብሮድካስቲንግ ሥራ አስፈጻሚነት ዘመናቸውን በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡

አቶ ወልዱ ይመስል አንድ የሬዲዮ ጣቢያ ተረክበው ተቋሙን በመሩበት የሥራ ዘመን ሬዲዮ ፋናን ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትነት አሳድገውታል፡፡ ጠንካራው የሚዲያ መሪ አስር ኤፍ ኤሞችን በክልል ከተሞች እንዲከፈቱ አድርገው በአዲስ አበባ የራሱን ህንጻ የገነባ ሚዲያ ፈጥረው በኢትዮጵያ በተወዳዳሪነቱ ስሙ የሚነሳውን ፋና ቴሌቨዥን እውን አድርገው የጀመሩትን የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለማጠናቀቅ ነው ሃላፊነታቸውን ያስረከቡት፡፡

ለእኚህ የተቋሙ ባለውለታ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች ባሳለፍነው ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸው ነበር፤ በፕሮግራሙ ላይ ለጠንካራ ተቋም ግንባታቸውና የምንመካበትን ሚዲያ ፈጥረዋል ለመባላቸው ያለ ግዴታ በተደረገ በጎ ፍቃድ ሠራተኛው ገንዘብ በማዋጣት ስጦታን አብርክቶላቸዋል፡፡

 

አቶ ወልዱ ይመስል 240 ሺ ብር ገደማ የብር ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን ተቋሙን የለቀቁ የቀድሞ ሠራተኞች ደግሞ የመታሰቢያ ስጦታ አበርክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ከሥራ ሃላፊነቱ የለቀቀ የሚዲያ መሪ በዚህ ደረጃ ሲሸኝ አቶ ወልዱ ምናልባትም የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀርም ይላሉ አስተያየታቸውን ለድሬ ቲዮብ የሰጡ የተቋሙ ባለሙያዎች፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top