Connect with us

ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ-በህመም ላይ ኾኖም የኢትዮጵያ ኩራት

ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ-በህመም ላይ ኾኖም የኢትዮጵያ ኩራት

ኢኮኖሚ

ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ-በህመም ላይ ኾኖም የኢትዮጵያ ኩራት

ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ-በህመም ላይ ኾኖም የኢትዮጵያ ኩራት፤
****
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም በኢትዮጵያ ገናና ከሚባሉት ብሔራዊ ፓርኮች አንዱ የሆነውና ቀደምቱን የኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ዛሬም በህመም ላይ ሆኖ የኢትዮጵያ ኩራት ነው ይለናል፡፡ የኦሞ ቆይታውን እንዲህ ተርኮታል፡፡ ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ኦሞ ታሟል፤ ስኳር ነው ህመሙ፡፡ ትልቅ ሀብት ነበር፡፡ ስኳር ፈልገን ተፈጥሮውን አጠፋነው፡፡ ትንሽ ነገር ስላጓጓን ትልቅ ነገር አበላሸን፡፡ እርግጥ ነው የታመመ ልማት ስኳር ጨውና ጮማ ላይ ዓይኑን ይተክላል፡፡

ኦሞ ነኝ፡፡ ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ለመድረስ የአምስት ፋብሪካ ኬላ ሰባት ጊዜ አስቆመኝ፡፡ እንዲህ ሆኖ ለመጎብኘት የሚመጣ እንግዳ የለም፡፡ የዓለም ሳፋሪዎች እንኳን እንዲህ ያለ ፍተሻ ሰው ሲያስነጥስ የሚወድቁ ስሱ የሆስፒታሊቲ ሳይንስ ማሳያዎች ናቸው፡፡

ፋብሪካዎቹን አየኋቸው፡፡ በርቀት ነው፡፡ እንዲህ ላለው ከተፈጥሮ የሚቃረን ልማት ወርቅ ቢበቅልበት አልጓጓም፡፡

የማልደብቃችሁ የፋብሪካው ጸጋ መንገዱ ነው፡፡ ኦሞ እንዲህ ሽር ብሎ መድረስ ከባድ ነበር፡፡ ሃና ቁርስ በላን፡፡ ከዚያ ምቹ በሚባለው መንገድ እዚህ ደርሰናል፡፡

የኦሞ ቅጥር ጀመረ፡፡ ተፈጥሮ መልኳ ተቀይሯል፡፡ መንገዱ ሁሉ መጤ አረም ነበር፡፡ እዚህ ሌላ መልክ እዚህ ሌላ ውበት እዚህ ሌላ ገጽ ተገለጸ፡፡ ኦሞ በታላቁ ወንዝ ስም የሚጠራው ታላቅ ብሔራዊ ፓርክ፡፡

ውበት ሙቀትን ድል ያደርገዋል፡፡ ሙቀቱ ከባድ ነው ግን የኦሞ መስክ ውበት እንዳላስበው አደረገኝ፡፡ እልል በይ ሜዳ እልል ብሎ ተቀበለኝ፡፡ የዝምታን ድምጽ ሰማሁ፡፡ የማማርን ዜማ አደመጥሁ፡፡ አፍ ካለው ሜዳ ተገናኘሁ፡፡ ኦሞ-ግዙፍ ውበት፡፡

መንገድ ብቻ ኦሞ ብዙ ያሳያል፡፡ ሳይፈልጉ ዓይን ከሁሉም አቅጣጫ ድንቅ እንሰሳ ይዞ ይመለሳል፡፡ ይህ ኦሞ ነው፡፡ እዚህ ኢንሹዎች ይርመሰመሳሉ፡፡ እዚህ ቀኑ የአራዊት ሌት ነው፡፡ እዚህ ብርቅ ነው የለም የሚባል የለም፡፡ ሁሉም በመንገድ ይታያል።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top