Connect with us

የወር አበባ መቆም በደም ሥር ጤና ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል – ጥናት

የወር አበባ መቆም በደም ሥር ጤና ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል – ጥናት
Photo: onsalus

ጤና

የወር አበባ መቆም በደም ሥር ጤና ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል – ጥናት

የወር አበባ ማየት ማቆም በሴቶች የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡

በተፈጥሮ ሴቶች የወር አበባ ማየት የሚያቆሙት በ45 እና 50 ዓመት መካከል ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኑ ይታወቃል።

ሰሞኑን ይፋ የሆነው አዲስ ጥናትም የዕድሜ መግፋትን ተከትሎ የሚከሰተው የወር አበባ መቆም የሴቶችን የደም ስር ጤና የሚያውክ መሆኑን አመላክቷል፡፡

 

ችግሩ ከነጭ ሴቶች ይልቅ በጥቁር ሴቶች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያወች ተናግረዋል፡፡

እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ በወር አበባ ወቅት በርካታ የምግብ መፈጨትና ጥቅም ላይ የመዋል ሁኔታ ይስተዋላል።

የልብ ህመም እና ተያያዥ በሽታዎች፣ በደም ቧንቧወች ላይ የቅባት መጠን መጨመር፣ የወገብ አካባቢ እና የምግብ መፈጨት ችግር ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች መሆናቸውንም ባለሙያወች ይናገራሉ።

በሌላ በኩል ከመጨረሻው የወር አበባ ዓመት በኋላ የሚከሰት የሆርሞን መለዋወጥ የደም ቧንቧ ጤናን የሚጎዳ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተካሄደው ጥናት የመጨረሻው የወር አበባ ከመምጣቱ በፊት የደም ወሳጅ ጥንካሬ በግምት 0 ነጥብ 9 በመቶ ሲሆን፥ ከዚያ በኋላ ባለው ዓመት ደግሞ ወደ 7 ነጥብ 5 በመቶ ከፍ እንደሚል ተመላክቷል።

ስለሆነም ጥናቱ ሴቶች የወር አበባ ማየት በሚያቆሙበት ወቅት የልብና የደም ቧንቧ ጤንነታቸው እየተባባሰ የሚሄድ መሆኑን በመረዳት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እደሚገባቸው ተጠቁሟል።

ምንጭ፡-https://www.medicalnewstoday.com

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top