Connect with us

ዛሬ የሬዲዮ ቀን ነው፤ ኑ የሬዲዮ ክብር በሬዲዮ በሞተበት ዘመን ስለ ሬዲዮ እናውራ

ዛሬ የሬዲዮ ቀን ነው፤ ኑ የሬዲዮ ክብር በሬዲዮ በሞተበት ዘመን ስለ ሬዲዮ እናውራ
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ዛሬ የሬዲዮ ቀን ነው፤ ኑ የሬዲዮ ክብር በሬዲዮ በሞተበት ዘመን ስለ ሬዲዮ እናውራ

ዛሬ የሬዲዮ ቀን ነው፤ ኑ የሬዲዮ ክብር በሬዲዮ በሞተበት ዘመን ስለ ሬዲዮ እናውራ፤ | ሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

“የት ሰማችሁ?” ስትባሉ “ሬዲዮ አወራ” ብላችሁ ማን ሞግቷችሁ ያውቃል? ምክንያቱም ሬዲዮ ነዋ፡፡ ሬዲዮ ይታመናል፡፡ በሬዲዮ ዝም ተብሎ አይወራም፡፡ ሬዲዮ እውቀት ነው፡፡ ሬዲዮ እውነት ነው፡፡ እጃችን ላይ ያለው ሰዓት ምን ቢነግረን የሬዲዮኑ ቅድሚያ ያገኛል፡፡

ዛሬ የሬዲዮ ቀን ነው፡፡ ዓለም ስለ ሬዲዮ ያወራል፡፡ ሀገራችንም የሬዲዮ ትዝታዎች እዚህም እዚያም በዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ እየተወሩ ነው፡፡ ብሔራዊ ሬዲዮም ቀኑን ዘክሯል፡፡ እርግጥ ነው ዛሬ ብዙ የሬዲዮ ጣቢያ አለን፡፡ ግን የትናንቱ የሬዲዮ ሞገስና ክብር አድማጩ ጋር አለን ብለን ብንጠይቅ መልሱ ዝም ነው፡፡

ዛሬ ከተደራሲው እውቀት በታች የሆኑ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ብዙ ናቸው፡፡ ዛሬ የትም የምንሰማው ነገር የሬዲዮ ሀሳብ ኾኗል፡፡ ዛሬ አንዳንድ የሬዲዮ ፕሮግራሞች አልባሌ ቦታ የመዋልን ያኽል ልጆቻችን እንዳይሰሟቸው የምንጠብቃቸው መጥፎ ድምጾች ኾነዋል፡፡

በዓለም ለዘጠነኛ ግዜ የሚከበረው የሬዲዮ ቀን ከዓለም ጋር ስናከብረው ዓለም ከሬዲዮ ያገኘውን ትርፍ እኛ አግኝተን ይኾን? አንድ የሚዲያ ባለሙያ አሁን ያለውን የሬዲዮ ኢንዱስትሪ ተመልክተው ምራቅና ምላስ ያለበት ሁሉ የሚገባበት ሲሉ ገልጸውታል፡፡

እርግጥ ሬዲዮን ያዋረደው ሬዲዮ ነው፡፡ ጥቂት የሬዲዮ ፕሮግራሞች ጥቂት የሬዲዮ ጋዜጠኞች ዛሬም እንደ ትናንቱ በሚከበረው የሬዲዮ ክብር ልክ እየደከሙና እየለፉ ይገኛል፡፡ ቴሌቨዥን ሲመጣ መታየት ብርቅ የኾነበት ማህበረሰብ ሬዲዮን ዝቅ አድርጎ መመልከት ጀመረ፤ ቀጠለና ሬዲዮን ማንም ያወራበታል የሚለው ያልተጻፈ ህግ ናኘ፡፡ ከዚያ ሬዲዮ ቀላል ነገር ሆነ፤ ያወራው ባይታመንም ያወራል፡፡ የሚናገረው ፍሬ ባይኖረውም ይደመጣል፡፡ ቀጥሎ ሬዲዮ ሱቅ ሆነ፤ ሰራ ሰራ ማድረግ የፈለጉ ሰዎች ከመንገድ ተቀላቀሉት፡፡

ዛሬ ሬዲዮ እምነት ያጣው በተናጋሪው ተግባር ነው፡፡ ዛሬ ሪዲዮ ቧልት ማድመጫ ይመስል ለዛው ጎምዝዟል፡፡ ጥቂት ጣቢያዎች በጣት በሚቆጠሩ ፕሮግራሞች የሚመሰገኑባት ሀገር ላይ መኖር ጀምረናል፡፡ ያ ሬዲዮን ከብቦ የማዳመጥ ባህል የጠፋው በሬዲዮ አዲስ እንደፈቀደው የተጓዘ ባህል ሳቢያ ነው፡፡

የሬዲዮን ቀን ስናከብር በሬዲዮናችን ከአርበኞች ቀን ይልቅ የቫላንታይን ዜማና ወሬዎች በናኙበት ሌላ ዘመን ነው፡፡ በሬዲዮ ትውልድ ስለመስራት ማሰብ አቁመናል፡፡ ትውልድ ለማደንዘዝ የሚደክሙ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ብዙ ደርዘን አልፈዋል፡፡ ያም ኾኖ የሬዲዮ ቀንን ስናከብር የሬዲዮ ክቡር ትዝታ የምንወዳቸው ጋዜጠኞች ለዛና የሞገዱ ፍቅር ልባችን ላይ ነግሶ ነው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top