Connect with us

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገቢዎች ሚነኒስቴር አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በአዲሱ ኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጁ ዙሪያ በተለያዩ ወቅት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተከታታይ ውይይት ማካሄዱን ገልጿል፡፡

ከውይይቱም የተገኙ ግብአቶችን በመጠቀም አስፈላጊው ማሻሻያዎች እንደተደረጉ የገለፀው ሚኒስቴሩ በተጨማሪም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ ማድረግ ያለባቸውን ቅድመ ዝግጅትና በአጠቃላይ በአዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ውይይት መደረጉን አስታውቋል፡፡

በውይይቱም የኤክሳይስ ታክስ ምንነትና ታሪካዊ ዳራ፣ ኤክሳይስ ታክስ የሚጣልባቸው እቃዎችና አገልግሎት ባህሪያት፣ ኤክሳይስ ታክስ የሚጣልበትና የማሻሻያው ምክንያት፣ የረቂቅ አዋጁ ዋና ዋና ገጽታዎች እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከአምራቾች ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ ደርሷል፡፡

ስለሆነም አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎም እንደሚጠበቅ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top