Connect with us

ፓርላማው የኤክሳይዝ ታክስ እና የጥላቻና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት መከላከል አዋጆች ሐሙስ ዕለት ያጸድቃል

ፓርላማው የኤክሳይዝ ታክስ እና የጥላቻና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት መከላከል አዋጆች ሐሙስ ዕለት ያጸድቃል
Photo: Facebook

ዜና

ፓርላማው የኤክሳይዝ ታክስ እና የጥላቻና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት መከላከል አዋጆች ሐሙስ ዕለት ያጸድቃል

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም መወያያ አጀንዳዎች የሚከተሉት ናቸው፣

1. የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ እና 1ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎች መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዓይነስውራን፣ለንባብ የእይታ ችግር ላለባቸው እና በመደበኛ የንባብ ስልት ለማንበብ አካላዊ ችግር ላለባቸው ሰዎች የቀለም ጽሁፍ ህትመት ስራዎችን ተደራሽነትን ለማመቻቸት የወጣውን የማራከሽ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣

3. የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአፍሪካ ህዝቦች እና ሰዎች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ አረጋዊያን መብቶች ፕሮቶኮል ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣

4. የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣

5. የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በውጭ አገራት ለተሰጡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ስምምነትን ለማጽደቅ የቀረበ ረቀቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣

6. የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣

7. የገቢ፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣

8. የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎችን ጥበቃና ድጋፍ የማድረግ የአፍሪካ ህብረት የካምፓላ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ማጽደቅ፣

9. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣

10. የማህበረሰብ ተፋሰሶች ልማት፣አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top