Connect with us

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል
Photo: Facebook

ዜና

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ለሰኞ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ አስተላለፈ፡፡

በተለይ በአዲስአበባ ከተማ 22 አካባቢ በሕገወጥ መንገድ ለቤተክርስቲያን መገንቢያ ቦታ ተይዟል በሚል በደንብ ማስከበር ስም በለሊት የተሰማሩ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሁለት ሰዎች ከተገደሉና በርካቶች ከቆሰሉ በኋላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና ምዕመናን በመንግሥት ላይ ቀድሞም ያሳደሩት ቅሬታ ማደጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

የሰማዕቱ ማለፍ ከተሰማ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ “ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል። የገደለም ፍርድ ይገባዋል።”( የማቴዎስ ወንጌል 5:21) ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 (በተለምዶ 22 አካባቢ) ውስጥ አዲስ መቃኞ ቤተክርስቲያን መሠራቱን መነሻ በማድረግ በአካባቢው በሚገኙ ምዕመናንና በከተማው የጸጥታ አካላት መካከል ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:00 በተፈጠረው አለመግባባት የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱና ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መጎዳታቸው መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top