Connect with us

የሸቀጦች ዋጋ አስወድደዋል የተባሉ ከ91ሺ በላይ ነጋዴዎችና ደላሎች ተቀጡ

የሸቀጦች ዋጋ አስወድደዋል የተባሉ ከ91ሺ በላይ ነጋዴዎችና ደላሎች ተቀጡ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የሸቀጦች ዋጋ አስወድደዋል የተባሉ ከ91ሺ በላይ ነጋዴዎችና ደላሎች ተቀጡ

ባለፉት 6 ወራት የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ለመከላከል በተሰሩ ስራዎች ከ90 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈጠረውን የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ለመከላከል በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚመራ ግብረ-ሀይል ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ ተዋቅሮ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በዚህም በህገ-ወጥ መንገድ ግብይቱን ሲያውኩ የነበሩ 91 ሺህ 739 ህገ-ወጥ ደላላዎችና ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብሏል፡፡

ግብረ-ሀይሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል150፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 17 ሺህ 182፣ በኦሮሚያ ክልል 14 ሺህ 961፣ በአማራ ክልል 53 ሺህ 126 እንዲሁም በደቡብ ክልል 6 ሺህ 320 የንግድ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች ወስዷል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ግብረ ሀይሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባደረገው ኦፕሬሽን በህገወጥ መንገድ ሲሸጥ የነበረ 59 መኪና አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 52 መኪና ጤፍና ስንዴ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

የተወረሰው ምርት በሸማች የህብረት ስራ ማህበራትና ኢት-ፍሩት በኩል ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጥ መደረጉን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#EBC

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top