Connect with us

የሜቴክ ሠራተኞች አመፁ

የሜቴክ ሠራተኞች አመፁ
Photo: Facebook

ዜና

የሜቴክ ሠራተኞች አመፁ

የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቢሾፍቱ ባስ መገጣጠሚያ ሠራተኞች የተገባልን የደሞዝ ጭማሪ ይፈፀምልን በሚል ምክንያት ከሦስት ሳምንት በፊት አራት አውቶቡሶችን አቃጠሉ።

ከ 10 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ በተደጋጋሚ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ለሠራተኞቹ ቃል ቢገባም መፈፀም አልቻለም።

በዚህ ምክንያት ተጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ፋብሪካው የተነሳ በተቃውሞ ግርግር መካከል ነው፣ መኪኖቹ በእሳት የተያያዙት።

ተገጣጥመው ሊሸጡ የተዘጋጁትን አራት አውቶቡሶች በሚቃጠሉበት ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ሠራተኛው መረባረቡን፤ ነገር ግን መኪኖቹ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን የዐይን እማኞች ገልጸዋል።

የሜቴክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መሐመድ እድሪስ ለአዲስ ማለዳ የድርጊቱን መፈጸም አረጋግጠው እስከ አሁን ግን በጉዳዩ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው የለም ብለዋል። (አዲስ ማለዳ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top