Connect with us

በኢፌዲሪ ፕሬዚደንት የተመራ ልዑካን ናይሮቢ ገባ

በኢፌዲሪ ፕሬዚደንት የተመራ ልዑካን ናይሮቢ ገባ
Photo: Facebook

ዜና

በኢፌዲሪ ፕሬዚደንት የተመራ ልዑካን ናይሮቢ ገባ

በፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራ ልዑካን በቀድሞ የኬንያ ፕሬዚደንት ዳንኤል ቶሮይቲች አራፕ ሞይ ብሔራዊ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ገባ።

ልዑካን ቡድኑ ዛሬ ጠዋት ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኬንያ ቱሪዝምና ዱር ኃብት ሚኒስትር ነጂብ ባላላና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም እና የኤምባሲው ዲፕሎማቶች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ለኬንያው ፕሬደዚንት ኡሁሩ ኬንያታ በላኩት የሀዘን መግለጫ በቀድሞ ፕሬዚደንቱ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በኢትዮጵያ ሕዝብና በራሳቸው ስም ገልፀዋል።

አራፕ ሞይ ለኬንያ ነፃነት ያደረጉትን ተጋድሎ አስታውሰውም ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ በቀጠናዊው በይነ-መንግስት ኢጋድ ምስራታ እንዲሁም ለአህጉራዊ ሰላምና ልማት ጉልህ ሚና እንደተጫወቱ ተናግረዋል።

ሁለተኛው የኬንያ ፕሬዝዳንት ቢያልፉም ለህዝባቸው እና ለአፍሪካ ደህንነት ባደረጉት በጎ ተግባር ሁሌም እንደሚታወሱ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ጠቅሰው ለኬንያውያን፣ ለኬንያ መንግስት እና የሟቹ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ዳንኤል ቶሮይቲች አራፕ ሞይ ከጥቅምት 04 ቀን 1971 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 21 ቀን 1995 ዓ.ም. ድረስ ኬንያን በርዕሰ ብሔርነት መርተዋል።(ምንጭ፡-በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top