Connect with us

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ተማፀኑ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ተማፀኑ
Photo: Facebook

ጤና

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ተማፀኑ

የኬንያው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ ተማፀኑ።

በኮሮናቫይረስ ፈጣን ስርጭት ስጋት የገባቸው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮሮና ቫይረስ በተስፋፋበት ወቅት ወደ ቻይና ጉዞ ማድረጉ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።

የኬንያው ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኡሁሩ የሚያሳስበኝ ደካማ የጤና ስርዓት ስላለን ኮሮና ቢከሰት ምን እንሆናለን የሚለው ነው ብለዋል።

አየር መንገዱ በዚህ ወቅት ወደ ቻይና መብረሩ ቫይረሱ አፍሪካን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል የሚሰጉት ፕሬዝዳንቱ ‹‹ እንደአገር የእኛ ጭንቀት ቻይና ቫይረሱን መቆጣጠር ይሳናት ይሆንወይ የሚለው አይደለም፤ ይልቁንም ጭንቀታችን የጤና ስርዓታችን ደካማ በሆኑብን አካባቢዎች ቫይረሱ ቢመጣስ የሚለው ነው›› ሲሉ ነው ስጋታቸውን የገለፁት።

በቻይና እና ራስ ገዟ ሆንግ ኮንግ 5 መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‹‹ወደ ቻይና የማደርገውን በረራ አላቋርም ይልቁንም በበረራዬ ላይ ለሰራተኞቼና ተጓዦች ከፍተኛ ጥንቃቄን አደርጋለሁ›› ሲል እንደማያቋርጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

በኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚመራው የዓለም ጤና ድርጅት ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎች ማቋረጥን አልደግፍም ማለቱም አይዘነጋም።

(አሐዱ ቴሌቪዥን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top