Connect with us

ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ-10 አጋጥሞ የነበረውን ችግር መፍታቱን አሳወቀ

ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ-10 አጋጥሞ የነበረውን ችግር መፍታቱን አሳወቀ
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ-10 አጋጥሞ የነበረውን ችግር መፍታቱን አሳወቀ

ማይክሮሶፍት በዊንዶስ-10 ውስጥ መሠረታዊ በሆነው የመተግበሪያ ሥርዓት /operating system/ አጋጥሞት የነበረውን ያልተጠበቀና መጠነኛ ችግር መቅረፉን አሳወቀ፡፡

በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የዊንዶውስ መፈለጊያ /windows search tool/ ረቡዕ ጥዋት አልሠራ እንዳላቸው ገልፀው ነበር፡፡
ተጠቃሚዎች እንደገለጹት የዴስክቶፕ መረጃ መፈለጊያ ትዕዛዝን ሲጠይቁ ባዶ ሳጥን ይሰጣቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ሪፖርት ከተደረገ ከሰዓታት በኋላ ካምፓኒው የአብዛኞቹን ተጠቃሚዎች ችግር መፍታቱን እና አንዳንድ ተጠቃሚዎች ሥርዓቱ መልሶ እንዲሠራላቸው ኮምፒውተራቸውን ዘግተው መልሰው መክፈት /restart/ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል፡፡

ዊንዶውስ 10 መተግበሪያ ሥርዓት /windows 10 operating system/ በዓለም ዙሪያ 800 ሚሊዮን የሚሆኑ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡
ማይክሮሶፍት ኩባንያ ባጋጠመው ችግር ምን ያህል ተጠቃሚዎች ችግሩ እንዳጋጠማቸው አልገለፀም፡፡

ተቋርጦ የነበረው ሥርዓት በዊንዶውስ ሥርዓት ውስጥ በሰፊው ለአገልግሎት ከሚውሉ መተግበሪያዎች አንዱ ሲሆን ተጠቃሚዎች ፋይሎችን፣ መተግበሪያዎችን፣ ኢ-ሜይሎችን እና ሌሎች ይዘቶችን በቀላሉ ከኮምፒውተራቸው ፈልገው ለማግኘት የሚያገለግል ነው፡፡
መተግበሪያው በተቋረጠበት ጊዜ ትልቅ ግራጫ ሳጥን ለተጠቃሚዎች ይታይ እንደነበረ ተገልጿል፡፡ ምንጭ፡BBC

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top