Connect with us

“ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር ሸጥኩት…”እናት

"ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር ሸጥኩት..."እናት
Photo: Facebook

ነፃ ሃሳብ

“ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር ሸጥኩት…”እናት

“ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር ሸጥኩት…”እናት – (ታምሩ ገዳ)

የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ህንዳዊቷ ፐሪማ ሰልቫም ከባለቤቷ ጋር በመሆን የቤተሰባቸውን ጉረሮ ለመድፈን በሸክላ ጡብ ስራ ላይ ተሰማርተው ቢታገሉም ባለቤቷ የራሱን ስራ ለመጀመር ወጥኖ የተበደረው ገንዘብን ለመክፈል ስለተሳነው እና ተስፋው ስለጨለመበት እንደ ምርጫ የወሰደው ነገር ቢኖር ባለፈው አመት የራሱን ህይወት ማጥፋት ነበር።

ከባለቤቷ ሞት በኋላ የኑሮ ጫና በሙሉ በትከሻዋ ላይ የወደቀው ፣በቀን ሁለት ዶላር ከሰማኒያ ሳንቲም(ስልሳ የኢትዮጵያ ብር አካባቢ )ተከፋይ የነበረችው ፐሪማ ሌላው ቀርቶ ልጆቿን እንኳን መመገብ ባልቻለችበት ወቅት በደረሰባት ህመም ለሶስት ወራት ከቤት በመዋሏ ያቺ ከእጅ ወደ አፍ ያልደረሰች ኑሮዋ መታወኩን ሰሞኑን ለቢቢሲ ተናግራለች።

አንድ ቀን ወደ ት/ቤት ሄዶ የነበረው የሰባት ዓመት ልጇ ወደ ቤተ ሲመለስ ምግብ እንደትሰጠ ወላጅ እናቱ ፐሪማን ቢጠይቅ “ምንም ምግብ የለም” የሚል ምላሽ ሲሰጠው አምርሮ ማልቀሰን የምታወሳው ወላጁ በጊዜው ከጥቂት የፕላስቲክ ቅርጫት ውጪ እንደ ወርቅ የመሳሰለ ዋጋ ያለው ጌጣጌጥ እና እቃ በቤቷ ውስጥ ታጣለች። በዚህ ብርቱ የመከራ ወቅት ከአይምሮዋ ውስጥ ዘልቆ የገባው ብቸኛ ሀሳብ ቢኖር በአቅራቢዋ ከሚገኘው የሴቶች እህቶች ጸጉርን አየላጨ ለተለያዩ ሴቶች በኤክስቴንሽንነት መልክ ለሚሸጠው መደብር ዞማ ጸጉሯን በሙሉ ለሁለት ዶላር መሸጥ እና ልጆቿም ሩዝ መመገብ ነበር።

ፐሪማ የኑሮ ውጣውረዱ ሲከፋባት እርሷም እንደ ባለቤቷ ህይወቷን ለማጥፋት በመሞከር ላይ ሳለች በአቅራቢያዋ የምትኖረው እህቷ በድንገት ደርሳ ታስጥላታለኝ።በዚህ መካከል እንደ እርሷ በታለያዩ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፎ ህይወቱ ከተቀየረው ብላ ሙርጋህን የተባለ የኮምፒውተር ባለሙያ ጋር ተዋወቁ ። ሶስት ልጆቿን ለማሳደግ ስትል በደረሰባት ችግር፣እንደ እናትነት የተጓዘቻቸውን መከራዎቿን የተረዳው የኮምፒውተር ባለሙያው ሙርጋህን ለጊዜው የተወሰነ ገንዘብ በመስጠት አሳዛኙ ታሪኳን በወዳጆች መገናኛ መረብ (ፌስ ቡክ) ላይ ከለጠፈው ከአንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ዶላር(መቶ ሀያ ሺህ የህንድ ሩፒ) ማግኘቱን አበስራት።

ባልጠበቀችው አጋጣሚ በእጅጉ የተደሰተችው እና ለተደረገላት ሰብአዊ እገዛም ያመሰገነችው ፐሪማ ለእራሷ እና ለልጆች የእለት ጉርስ መግዣ፣ ከፊል እዳዋምን ማቃለያ ገንዘብ ካገኘች በኋላ የተቀረው እዳዋን ቀስ በቀስ ( በእየወሩ አስር ዶላር) ለመክፈል እንደምትሞክር በመወሰን ፣ የፌስ ቡክ እርዳታው እንዲቋረጥ በመጠየቅ “ከዚህ በሁዋላ ኑሮ የቱንም ያህል ቢከብድብኝ እንደ ባለቤቴ ተስፋ በመቁረጥ ህይወቴን ለማጥፋት መሞከር ትልቅ ስህተት መሆኑን ተምሬያለሁ፣የቀረብኝ እዳንም ለመክፍል ድፍረት አግኝቻለሁ” በማለት ብሩህ ተስፋ መሰነቋን እና ሰው ለሰው መደሐኒትነቱን መግለጿን ቢቢሲ በአስተማሪነት ዘገባው አቅርቦታል።

እዚህ ላይ ህንዳዊቷ ፐሪማን የመሳሰሉ ስለልጆቻቸው ሲሉ መካራዎችን የሚጋፈጡ ፣ አሳዛኝ እና አስተማሪ ገድል ያላቸው ፣ነገር ግን ብዙ ያልተወራላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን እናቶች መኖራቸውን አሌ አይባልም ።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

 • የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት

  ባህልና ታሪክ

  የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት

  By

  የሚያዚያ የታሪክ ኩነቶች-እስከ መቅደላ መስዋዕትነት (ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የወርሃ ሚያዚያ ኩነቶችን ከታሪካችን ትዝታዎች እየጨለፈ እስከ...

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤ ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  ነፃ ሃሳብ

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  By

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን...

 • የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  ነፃ ሃሳብ

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  By

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ ሰባት ቁጥርና ሕይወት፤ (አፈወርቅ ልሣኑ ~ ድሬቲዩብ) ሰባት ቁጥር...

 • ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release) ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release)

  ነፃ ሃሳብ

  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release)

  By

  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release) “መንግስት የህግ...

To Top