Connect with us

ኢትዮ ቴሌም በግማሽ ዓመት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ዛቀ

ኢትዮ ቴሌም በግማሽ ዓመት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ዛቀ
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኢትዮ ቴሌም በግማሽ ዓመት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ዛቀ

ባለፉት 6 ወራት 22.04 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም የ6ወር አፈፃፀሙን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ላይ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት ባለፉት 6ወራት ድርጅታቸው የ22 ነጥብ 04 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት ችሏል።

እንደ ወ/ት ፍሬ ህይወት ገለፃ ትርፉ የዕቅዳቸውን 104 በመቶ ማሳካት የቻሉበት ነው፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ብልጫ አሣይቷል።

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አባባል ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹን ብዛት 45.6 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን ይህም የዕቅዱን የ99 በመቶ ያህል ነው። የደንበኞች ቁጥርም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ10.9 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።(ኢፕድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top