Connect with us

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ተመራማሪ ሮቦት ልትሰራ ነው

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ተመራማሪ ሮቦት ልትሰራ ነው
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ተመራማሪ ሮቦት ልትሰራ ነው

በምድረ ካናዳ የሀምብር ኮሌጅ ተመራማሪ የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ማርያማዊት ወንድወሰን ደምሴ አዲስ አበባ ተወላዳ ያደገች የ23 ዓመት ወጣት ናት፡፡ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትዋን የተከታተለችው በመሀል አዲስአበባ በሚገኘው እና የልጃገረዶች ብቻ መማሪያ በሆነው ናዝሬት ትምህርት ቤት ነበር፡፡

ወጣት ማርያማዊት የሁለተኛ መልቀቂያ ፈተናን በከፍተኛ ማዕረግ ውጤት አጠናቅቃ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ወርክ የትምህርት ክፍል ተመድባ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ሳለች እ.ኤ.አ በ2015 የነጻ ትምህርት ዕድል አግኝታ ወደካናዳ ተጓዘች፡፡

ኢትዮጵያዊቷ ማሪያማዊት እንደ አብዛኞቹ የአገሯ ልጆች እውቀት የእድገት መሰላል መሆኑን በመረዳት አካዳሚያዊ ብቃቷን ለማስመስከር በጆርጅ ብራውን ኮሌጅ ለአንድ ዓመት የሽግግር ትምህርቷን ተከታትላ በአጥጋቢ ውጤት እንዳጠናቀቀች በልዩ የሒሳብ ተሰጦዋ እና አሁን የደረሰችበት አቅጣጫ አመላካች አጋጣሚ ፈጠረላት፡፡

እርሱም በወቅቱ የሒሳብ ትምህርት አስጠኚዋ(Tutor) የነበሩ አንዲት መምህርት ማሪያማዊት ጊዜው ጎበዝ ተማሪ በነበረችበት ከሕብረተሰብ ሳይንስ ትምህርት(Social Science) ወደ ተፈጥሮ ሳይንስ(Natural Science) የትምህርት ዘርፍ ብታዘነብል ብዙ ውጤቶችን ልታገኝበት የሚያስችላት ያልተገለጠላት እውቀት እንዳላት አረጋገጡላት።

የእውቀት እናቷ የሆኑት የመምህርቷን ምክርን በሚገባ የተቀበለችው ወጣትተማሪው ማሪያማዊትም ባገኘችው እድል እና አጋጣሚውንበሚገባ በመጠቀም በሃምበር ኮሌጅ ውስጥ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ምህንድስና ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት በመግባት ሮቦቲክ ኤንድ አውቶሞቲቭ አፕላይድ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት በመከታተል በትምህርት ቆይታዋ ባሳየችው ልዩ ጥረት እና በገኘችው ከፍተኛ ውጤት የተነሳ ይባርት ፋሚሊ ነጻ የትምህርት እድል /እስኮላር ሽፕ /አሸናፊ ለመሆን ከመብቃቷ በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት በተማረችው የሮቦቲክ ምህንድስና ትምህርት ወጣት ተመራማሪ በመሆን እርሷን የመሰሉ ወጣት ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ትገኛለች።

ሁሌም ለትምህርት ልዩ ቦታ የምትሰጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ተመራማሪዋ ማሪያማዊት ቀደም ሲል በኮሌጅ ተማሪዎች መካከል ተካሄዶ በነበረ የሜጋትሮኒክስ ውድድር ሁለተኛ የወጣች ሲሆን የፊታችን ሚያዚያ /ሜይ ወር በከፍተኛ ክብር እና ማእረግ ትመረቃለች ተብሎ ይጠበቃል።

ከአካዳሚክ ትምህርት በተጓዳኝነት ለሙዚቃ ልዩ ፍቅር ያላት ወጣት ተመራማሪዋ ማሪያማዊት ወንደሰን ደምሴ በኢትዮጵያ በነበረችበት ወቅት ከታዋቂው የጃኖ የሴቶች ባንድ ውስጥ በጊታር ተጨዋችነት ባሻገር በሕይወት ማሞ በሚመራው የሙዚቃ ትምህርት ቤት የፒያኖ መምህርት በመሆን እንዳገለገለችከቅርብ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ተመራማሪዋ ማርያማዊትን:በቅርብት :የሚያውቋት: ምንጮች ለእውቀት መጨረሻ የለውም የሚል ፍልስፍና እና መርህን የምትከተለው ወጣት ተመራማሪዋ ማሪያማዊት በቅርቡ “ፋሚ ሮቦት ለሀገር ኩራት”የሚል ስያሜ ያለው ሮቦትን በመስራት የአገሯ ኢትዮጵያን ስም የምታስጠራ ወገኖቿንም የምታኮራበት መድረክን  ይፋ እንደምታደርገው ገልፀዋል::

(ከኤሊያስ አወቀ፣ቶሮንቶ ፣ለሕብር:ሬድዮ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top