Connect with us

በፒያሳ ሰባት ሱቆች በእሳት ጋዩ

በፒያሳ ሰባት ሱቆች በእሳት ጋዩ
Photo: Facebook

ዜና

በፒያሳ ሰባት ሱቆች በእሳት ጋዩ

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ፡፡

4 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በተከሰተው በዚህ እሳት አደጋ ሰባት ሱቆች ላይ ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።

የእሳት አደጋው 4 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን፥ የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ስራ አመራር ኮሚሽን በስፍራው በመገኘት እሳቱ ተጨማሪ አደጋ ሳይስከትል መቆጣጠር መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

በዚህ አደጋ በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ እና የአደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

አደጋው በተከሰተበት ስፍራ ላይ ምግብ ቤቶች ፣ የአልባሳት፣ የመነጸር እና የኮስሞቲክስ ሱቆች እንደነበሩ ነው የተገለጸው፡፡(ፋና)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top