Connect with us

እነእስክንድር ነጋ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ሊመሰርቱ ነው

እነእስክንድር ነጋ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ሊመሰርቱ ነው
Photo: Facebook

ዜና

እነእስክንድር ነጋ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ሊመሰርቱ ነው

እነእስክንድር ነጋ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታን በመጪው እሁድ ሊጀምሩ ነው፡፡ ለሳምንታት በዩናይትድ ስቴትስ እየተዘዋወሩ ሕዝባዊ ምክክር ሲያደርጉ የሰነበቱት ‹‹የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት›› ሰብሳቢ እስክንድር እና ልዑካቸው ከሲቪክ ማኅበርነት ይልቅ በፖለቲካ ፓርቲ ተደራጅቶ መታገልን ሲያነሱ ነበር፡፡

ይህን ተከትሎም በመጪው እሁድ ጥር 3 ቅድመ እውቅና ለማግኘት የሚያስችላቸውን ጉባኤ የሚያደርጉ ሲሆን፤ ከሰኞ ጀምሮ በምርጫ ቦርድ እውቅና ለማግኘት የሚያስቻላቸውን ሥራ እንደሚጀምሩ እስክንድር ነጋ ተናግረዋል፡፡

መጋቢት 2/2011 የተመሰረተው የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ‹‹ባልደራስ›› እስክንድርን ሰብሳቢ ጋዜጠኛ ኤርሚያስ ለገሰን ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

(አሐዱ ቴሌቪዥን)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top