Connect with us

ምክር ለወንደ(ለሴተ) ላጤዎች!

ምክር ለወንደ(ለሴተ) ላጤዎች!
Photo: Facebook

ጤና

ምክር ለወንደ(ለሴተ) ላጤዎች!

#ምክር_ለወንደ(ለሴተ)_ላጤዎች!

እንግዲህ በዓል ነው፡፡ በበዓል ዋዜማ ዘና ፈታ ማለት የተለመደ ነው፡፡ ይኸም ሆኖ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረሥጋ ግንኙነት ከማድረግ መታቀብ ከጤና አንጻር ተደጋግሞ የሚመከር ነው፡፡ የግድ ሲሆን በአግባቡ ኮንደም መጠቀም ብልህነት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ መዘናጋት ካጋጠመ በሚል ማሪስቶፕ ኢንተርናሽናል ተከታዩን ምክር ይለግሳል፡፡

“ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብል” ድንገተኛና ጥንቃቄ በጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ምክንያት ያልታቀደ እርግዝና እንዳይከሰት ያግዛል። ውጤታማ እንዲሆን ግንኙነቱ በተደረገ በአምስት ቀናት ውስጥ መወሰድ አለበት። ግንኙነቱ ከተደረገ ወዲያው መወሰዱ ውጤታማነቱ ላይ የተሻለ ለውጥ ይኖረዋል። ይህም የሚሆነው የእንቁላሉን መለቀቅ በማስቆም ወይም በማዘግየት ሲሆን ቀድማ እርጉዝ ለሆነች ሴት ግን ይህ አይሰራም።

ልብ በይ!.. የእርግዝና መከላከያ አማራጮችን እንደድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ መጠቀም ትችያለሽ። ለምሳሌ ሉፕ (IUD) መጠቀም ይቻላል። የድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብል ከስሙ እንደምረዳው ከአቅም በላይ የሆነ ድንገተኛ የግብረሥጋ ግንኙነት ሲያጋጥም የሚወሰድ የእርግዝና መከላከያ ነው። ድንገተኛ እና ጥንቃቄ የጎደለው የግብረሥጋ ግንኙነት አጋጣሚዎች ይፈጠራል ብለው የሚያስቡ ከሆነ ሌሎች የረጅም ወይም የአጭር ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን ቢጠቀሙ ይመከራል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top