Connect with us

ባለሥልጣኑ የኮድ 3 ሰሌዳ እጥረትን ፈትቻለሁ አለ

ባለሥልጣኑ የኮድ 3 ሰሌዳ እጥረትን ፈትቻለሁ አለ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

ባለሥልጣኑ የኮድ 3 ሰሌዳ እጥረትን ፈትቻለሁ አለ

በአዲስ አበባ ከተማ የታየውን የኮድ 3 የመኪኖች ታርጋ እጥረት ለመፍታት በተሰራው ስራ ችግሩን መቅረፍ መቻሉን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ ለኢትየጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ተከስቶ የነበረውን የኮድ 3 ታርጋ እጥረት ለመፍታት መስርያቤታቸው ስራዎችን ሰርቷል፡፡

አቶ አብዱልበር ገለፃ አዲስ አበባ ውስጥ በተለይም በኮድ 3 ላይ የታየ የታርጋ እጥረት መኖሩን ተናግረው ለዚህም ከአንድ ወር ወዲህ የተከሰተውን የጥሬ እቃ እጥረት በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለፃ መስርያ ቤቱ በአሁኑ ሰአት በቀን ከ 500 እሰከ አንድ ሺህ ታርጋዎችን ለማምረት የሚያስችል አቅም ያለው ሲሆን ከሁለት ወራት በኋላም በቀን ከሁለት ሺህ እስከ ሶስት ሺህ ታርጋዎችን ማምረት የሚያስችሉ አዳዲስ ማሽኖችን ከውጪ ያስመጣል፤ በሂደትም የሚገጥሙ እጥረቶችን ለመፍታት የሚያስችል ብቻ ሳይሆን ከ100 ሺህ በላይ ታርጋዎችን ለማምረት እቅድ እንዳለም ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሩ ተከስቶ የነበረው የኮድ 3 ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እጥረት መፈታቱን ገልጸዋል።

(ምንጭ ኢፕድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top