Connect with us

የ20 አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክች ጨረታ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው

የ20 አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክች ጨረታ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው

ኢኮኖሚ

የ20 አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክች ጨረታ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ መንዶች ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት ግንባታቸውን ለማስጀመር በዕቅድ ከያዛቸው በርካታ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል 20 የሚሆኑት የጨረታ ሂደታቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ባለስጣኑ በተያዘው በጀት ዓመት40 የሚሆኑ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን የጨረታ ሂደታቸውን አጠናቆ ወደ ግንባታ ስራ ለማስገባት በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 20 የሚሆኑት የመንገድ ፕሮጀክቶች የጨረታ ሂደታቸው በመገባደድ ላይ ይገኛል፡፡ ቀሪዎቹ 20 የሚሆኑት ደግሞ በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሂደታቸው ይጀመራል፡፡ በአሁኑ ወቅት የጨረታ ስራቸው ተጠናቆ ወደ ግንባታ ይገባሉ ተብሎ ከሚጠበቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል፡-

• ከአየር ጤና -ወለቴ
• የ ቢ-2 ኮሊዶር የፈጣን አውቶቢስ መስመር ግንባታ
• ከአውግስተ- ወይራ መጋጠሚያ
• በሻሌ ኮንደሚኒየም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት
• ከፉሪ- ሀና ማሪያም
• ወታደር ኮንደሚኒየም ሳይት

• ቦሌ ጃክሮስ
• ንፋስ ስልክ ኢንዱስትሪ መንደር
• ቦሌ አራብሳ ኮንደሚኒየም ሳይት
• ጨሬ ኮንደሚኒየም ሳይት
• የአቃቂ ድልድይ

• ቦሌ አራብሳ እና ቦሌ ቸሪ ኮንደሚኒየም የመንገድ ዲዛይንና የግንባታ ስራ
• ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም ሳይት
• ድልድዮች
• ቦሌ አራብሳ 6ኛ መንገድ

• ቦሌ አራብሳ ሎት 11 እና በመሀል አዲስ አበባ የተለያዩ ቦታወች ላይ የሚሰሩ የመንገድ ዳር መብራቶችን ማዘመን የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች አጠቃላይ ከ67 ኪ.ሜ በላይ ርዝመትና በአማካኝ ከ10 ሜት እስከ 40 ሜትር ስፋት የሚኖራቸው ይሆናል፡፡ በከተማዋ የሚጀመረው የፈጣን አውቶቢስ መስመር ግንባታም ለከተማዋም ሆነ ለሀገሪቱ የመጀመሪያ ከመሆኑም ባሻገር አሁን ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍና ዘመናዊ የብዙሀን ትራንስፖርትን ለማስፋፋት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

እነዚህ በጨረታ ሂደት ላይ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ አሁን ላይ እየታየ ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማሻሻልና የከተማዋን የመንገድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ በአዲስ መልክ የሚገነቡ ናቸው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ መንገዶቹ ሲጠናቀቁ የከተማዋን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድግ ጉልህ ሚና የሚኖራቸው ሲሆን መዲናዋም ውብና ማራኪ የሆነ ከባቢያዊ ገፅታ እንዲኖራት ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡(አ/አ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top