Connect with us

ጭንቀትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል ?

ጭንቀትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል ?
Photo: Facebook

ጤና

ጭንቀትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል ?

ጭንቀት የሰውነትን ተፈጥሯዊ ሚዛን የሚያዛባ እና ነገሮች አልያም ደግሞ ሁኔታዎች ከቁጥጥር በላይ እንደሆኑ ሲሰማን የሚፈጠር ስሜት ነው ፡፡

ጭንቀት ኑሮን ከማቃወስ ባሻገር የሰውነት ድካም፣ ከፍተኛ የራስ ምታት፣ የደም ግፊት መጨመር እና ለሌሎች ህመሞች ይዳርጋል፡፡

ታዲያ ጭንቀትን እንዴት ማስወገድ አልያም ደግሞ እንዴት መቀነስ ይቻላል የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው፡፡

ጭንቀትን ለመከላከል ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መፍትሄዎች መጠቀም መልካም መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ፤

ለመዝናናት መሞከር

ጭንቀትን ለማስወገድ ለመዝናናት መሞከር አንዱ መፍትሄ ሲሆን፥ ይህም ሙዚቃ ማዳመጥ፣ መመሰጥ፣ ትንፋሻችንን ወደ ውስጥ በመሳብ ራስን በማዝናናት ጭንቀትን ማስወገድ ይቻላል፡፡

በቂ እንቅልፍ መውሰድ

እንቅልፍ ጭንቀትን ለማስወገድ ሌላው አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ፀጥታ ባለበት፣ መብራት እንዲሁም ስልክን በማጥፋት በቂ እንቅልፍ በመተኛት ጭንቀትን መከላከል እንደሚቻል ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡

በሞቀ ውሃ ገላን መታጠብ ወይም ተዘፍዝፎ መቆየት

በሞቀ ውሃ ገላን መታጠብ አጥንት እዲነቃቃ በማድረግ ከድብርት ስሜት መውጣት እንዲቻል አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

አትክልት መመገብ

የጭንቀት ስሜት ሲፈጠር በተለይ ፍራፍሬዎችን በብዛት በመመገብ ከጭንቀት በፍጥነት ማገገም ይቻላል፡፡

ምንጭ ፦http://www.buzznoble.com

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top